Friday, April 21, 2017

ሸነግ ደርቢ

 ሸነግ ደርቢ

1. ሸነግ ደርቢ ዛሬ ነው :)



2. የሸነግ አባል ለሆናችሁ በሙሉ "አግ7" የሚለውን የጥምረት ስም ስታዩ ፓስዎርድ በቀላሉ እንዳይሰረቅ የተዘየደ የቃላትና የቁጥር ጥምረት መስሏችሁ እንዳትሸወዱ ይሁን :P




3. የሽሮ ሜዳ፣ የተክለሃይማኖትና፣ የ22 ማዞሪያ ልጆች ከ multi-ethniኩ ሸነግ ተገንጥለው የethno-nationalist እንቅስቃሴ ለመጀመር አስበዋል ይባላል። ሸነግ እንዲህ ብሎ ይጠይቃቸዋል:- እናንተ ብሔር ናችሁ፣ ብሔረሰብ ናችሁ፣ ወይስ ህዝብ?

4. ተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠየቀውን ጥያቄ በትክክል የመለሰ ሰገጤ አውቶማቲካሊ የሸነግ አባል ይሆናል :)



5. ሸነግ ቢሸፍት ከወለቴ አያልፍም እያሉ ሰገጤዎች ያሙናል አሉ!

ጥራኝ እንጦጦ ፣ ጥራኝ ወጨጫ፣
አንዱን በእርግጫ፣ አንዱን በጡጫ።
የሚለውን የትግል እንጉርጉሯችንን አልሰሙምን?

6. አትረፍ ያለው ሰገጤ ካፊቴሪያ ገብቶ "አንድ ወፈር ያለ ሻይ በስቲኪኒ" ያዛል። ወግ አይቀርም መቼም :P

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”