Friday, April 21, 2017

ስብ-ሰባ (ስብሰባ)

(Kuku Adem)
* * * * *
(ስብ-ሰባ(ስብሰባ) ላይ ነበርን)
-
ኪራም (የስራ ባልደረባዬ) ሁሌም ስብሰባ ልንገባ ስንል ይጸልያል....
እኔ: ኪራ ለምንድን ነው ግን ስብሰባ ከመባታችን በፊት ሁሌ የምትጸልየው?
Kiram Kebede: ቸርች ያኔ ልጅ እያለን ሁሌም ከመተኛታችሁ በፊት ጸሎት አድርጉ ተብለን ስለተማር ነዋ !
- - - - - -
(በስብሰባው መጨረሻም)
-
አለቃችን: ኩኩ ከዛሬ ስብሰባችን የቀሰምሽው አዲስ ነገር ካለ እስቲ አካፍይን?
እኔ: አለ እንጂ በደንብ...በእውነቱ ዛሬ አይኔን ሳልጨፍን እንቅልፍ መተኛት እንደምችል ከኪራም ተሞክሮ ትልቅ ልምድ ቀስሜያለሁ!
-
ስብሰባን የፈጠረውን ሰገጤ ገሎ አንገቱን አንጠልጥሎ ላመጣላት ሰው ሸነግ ወረታውን ትከፍላለች ሲል የሸነግ ዋና ሊቀመኳስ Eyob Mihreteab Yohannes...አስታውቋል።
-
(ምፅ ምፅ...ስብሰባ!)

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”