Friday, April 21, 2017

የመጀመሪያይቱ

ይህ የቀልድ ሳይሆን እውነተኛ ግጥም ነው፡፡ ግጥሙን አሳትሞት፣ የዱሮው የ2004 ዓ.ም ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ነው ያነበብነው ፡፡
-
ሰገጤ ምን አይነት ዥልጥ ፍጥረት መሆኑን እርስዎ አንብበው ይፍረዱ፡፡ ይዝናኑ፡፡
-
“የመጀመሪያይቱ”
መጣች ዲሞክራሲ እንደ ሃረግ ተመዛ
ሳይበሉ ሚያጠግብ እንጀራዋን ይዛ
እንኳን ደህና መጣሽ ካለሽበት ሃገር
እኒያ ጠላቶችሽ ትቅር ብለው ነበር
መጣች ይች ስመጥር በሸዋ በትግሬ
እዮሃ አበባዬ መስቀል ገባ ጥቁሬ
ከወዲያኛው አለም ከተንጣለለው
ነጭ ጥቁር ቢጫ ከመላው
ደቡብና ምስራቅ ምእራብ ሰሜን ሳይቀር
ተስፋ ደማሚቱ የፈረንጅ ሃገር
እንደጣይ አብርታ ትታየኝ ጀመር
መጣሁ ብትለነ እኛም አይዞን አልናት
ይቺ አዲስ ጨረቃ የምርጫ አብነት
ላጣ ለነጣው ሁሉ ደረሰችለት
መጣች ዲሞክራሲ እንደ ሃረግ ተመዛ
ሳይበሉ ሚያጠግብ ህገ መንግስት ይዛ
ይች አመለ ሸጋ የግሪክ ዘፈን
የእንግሊዝ የአሜሪካ ፍቅር ሰመመን
የሞስኮብ በሽታ የዛሬው ሳይሆን
መጣች ዲሞክራሲ ለኛም ቀን አለን
እልል በሉ ጎበዝ እልል በሉ ሴቶች
ሰላም ናፋቂዎች ፍትህ ፈላጊዎች
ተምእራብ ገስግሳ ዲሞክራሲ መጣች
እንደ ጣይ ወጣች አበራች ለሁሉም
እንዲህ ነው መታደል ያላየነው የለም
አልቀ ደቀቀ በጎሳ መጋጨት
ቋንቋ መነፈጉ የጨቋኞች ስርአት
ተብነሽነሽ አበሻ ተውረግረግ ኮበሌ
ለዚህ አዲስ ብርሃነ ለዚህ አዲስ ቆሌ
ከንግዲህ አበቃ የጥይት ጩ£ት
ወንተረጂም ቡስጣሙ ይቅለለው መሬት
እሷን ሳያገኛት ለተሸኘባት
የኛን ዲሞክራሲ የኛን እመቤት
ካሁን ወዲያ ላይኖር ችግርም ጭንቀት
መጣች ዲሞክራሲ እንደ ሃረግ ተመዛ
ሳያበሉ የሚያጠግብ ህገ መንግስት ይዛ፡፡
-
(ከአስራት እንለይ “የመጀመሪያይቱ” መድብል የተገኘ፡፡ - ሪፖርተር ጋዜጣ፣ መጋቢት 5 ቀን 2004)

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”