Friday, April 21, 2017

ያሸንፋል!

*** በሜትሮፓሊታን አስተሳሰብ የነቃ፣ በሸነግ የተደራጀና፣ ፌስቡክን የታጠቀ ጀለስካ ሁሌም ያሸንፋል። ***
-
እውነት እውነት እልሃለሁ። ይህንንም ያንንም ብሄር መገንጠል፣ የፕጋፔም ይሁን የጭጋፌ ሪፐብሊክ የመመስረት ቅዠት ይኖርህ ይሆናል። ይህንን የልጅ ቅዠት ከመቃዠትህ በፊት ግን እውነተኛ የልጅነት ህልም ነበረህ። ይህ የልጅነት ህልም በብሄር፣ በሃይማኖትና በመደብ እንዲሁም በአልጋ መለያየት የማይለያይ፣ ሁሉንም ሰገጤ አንድ የሚያደርግ እውነተኛና ብቸኛ ህልም ነው። ይህ ህልም አንድና አንድ እንደሆነ አንተም እኔም እናውቀዋለን: ስናድግ የሸገር ልጅ መሆን! ይህንን ዶክተርና ፓይለት ከመሆን በበለጠ የተመኘነውን ህልም ሊያሳካ ሸነግ ተቋቁሞልናልና ባላገሮች ደስ ይበለን።
-
ባላገር ሆይ፣ "እኔ ስፈጠር ሰገጤ ነኝና እንዴትስ ሸነግ መሆን ይቻለኛል?" በማለት እንዳትሰጋ። ሲጀምር ይሄ "አልችልም" የሚለው ባላገራዊ አመለካከት ሰገጤነት ያመጣው ቅጭት (ሰገጤአዊ መቀጨት) ነው። ሸነግ ትሩሊ ዲሞክራቲክና ሜትሮፖሊታን ከመሆኑ የተነሳ በሶሻል ሞቢሊቲ ከምር ያምናል። እንደ ናሁሰናይ በላይ መቀሌ ተወልደህ አድገህ፣ የ"መቐለ" መርከብ ስም ዘመቻ እየመራህ የነበርክ የፌደራሊዝም (ያው የሰገጤነት) ምሁር እንኳ ብትሆን፣ ሂስህን ውጠህ፣ እንደ ሜትሮፓሊታን ማሰብህን የሚያሳይ ሸነጋዊ የፌስቡክ ማኒፌስቶ በማስረጃ ካቀረብክ፣ ድል ያለ ሸገራዊ አቀባበል ይደረግልሃል። :-)
-
እንደ አቤል አባተ በሸገር አውትሰከርት (ኮተቤ) ያደግክ ከፊል-ሰገጤ ብትሆን እንኳ አፈፃፀምህ ታይቶ፣ በከተማዊ ሚዛን ተመዝነህ፣ "እግዜር እጁን ታጥቦ የሰራው፣ የእውቀት አድማሱና ጸባዩ በኒው ዮረክ ስቶክ ማርኬት የዋጋ ልኬት መሰረት45 ሚልዮን ዶላር የሚመዘነው" ተብለህ ሸነግን ትቀላቀላለህ። :-)
-
እንደ ማስሬ ከሸገር መቶ ኪሎሜትር ርቀት ብቻ በምትገኝ የገጠር ቀበሌ ተወልደህ፣ በየቀኑ ተራራ ላይ እየወጣህ ሸገርን አማትረህ እያየህና እየናፈቅክ ያደግክ፣ ስታድግም ከዚህ ህልም ጋር ኮምፓተብል የሆነ ሜትሮፖሊታን ስታቸር ካዳበርክ የሸነግ አመራር አባል ሁላ ልትሆን ትችላለህ። :-)
-
ባላገር ሆኖ መወለድ የእድል ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ባላገር ሆኖ መሞት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው!:-)
-
ሸነግን በመቀላቀል የልጅነት ህልማችንን እናሳካ። "ጓድ" ከሚለው ጉደኛ መጠርያ ተላቀን "ጀለስካ" የምንባባልበት ዘመን እሩቅ አይሆንም!
-
በሜትሮፓሊታን አስተሳሰብ የነቃ፣ በሸነግ የተደራጀና፣ ፌስቡክን የታጠቀ ጀለስካ ሁሌም ያሸንፋል!

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”