(By: Adugna Lelisa Sime)
* * * * *
ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከተ አጭር መግለጫ
ሚያዝያ 14 ቀን 2009ዓም
.
በቅርቡ አንዳንድ የአገራችን ክልሎች(በተለይም የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች) የአገሪቱን ህገ መንግሥት ባልተጣረሰ መልኩ ኢኮኖሚያቸውን ለመገንባት፣አቅማቸውን ለማሳደግ እና የህዝቦቻቸውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወኑ ያሉትን ተግባራት የሸነግ ስብስብ በትኩረት የሚመለከት እና የሚደግፍ ቢሆንም ይህ አካሄድ በክልሎች መካከል አላስፈላጊ ፉክክር እንዳያመጣ እና አገራዊ አንድነቱን የበለጠ ስጋት ላይ የሚጥል እርምጃ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ከወዲሁ አበክረን ለማሳሰብ እንወዳለን።