Friday, April 21, 2017

ሂሥ እና ግለ ሂሥ

ሂሥ እና ግለ ሂሥ በሸነግ ምክር ቤት...

(ክቡር መተኪያ ሀይለሚካኤል)

ባሣለፍነው ሣምንት የሸነግ ጠቅላላ ጉባኤ በአባላቱ በፖሊት ቢሮ ቊዋሚና (ቃሚና) በተጠባባቂ አባላቱ እንዲሁም በሥራ አሥፈጻሚው አባላት ላይ ሂሥና ግለ ሂሥ ሢያካሂድ በመቆየቱ እንቅሥቃሤው በሠገጤዎች የተገታ የመሠላቸው አንዳንድ በውጭ ሀገር በርገራቸውን የሚበሉና ድርጅታችንን ለማተራመሥ የሚፈልጉ ጸረ ሸነጎች ፕሮፓጋንዳ እየነዙ እንደሆን ደርሠንበታል..


-

ድርጅታችን ሸነግ ባሣለፍነው ሣምንት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤውና የገቢ ማሠባሠቢያ ፕሮግራሙ ሀሪፍ ዝግ ዘግቱዋል..ሸቅሉዋል..
በሂሥና ግለ ሂሡ ደግሞ በሸነግ ውሥጥ መካከለኛ አምባገነንነት እየተሥፋፋ መምጣቱ ይህም የግንባሩን እድገት የሚያሣይ እንደሆነ በአንጎላ በናሚቢያ በቺሊ እንዲሁም በደቡብ ሡዳን የሚገኙ እህት የነጻነት ታጋዬች በመግለጫቸው አሣውቀዋል..እናም በሥብሠባው ላይ ሥለ እህት ድርጅቶች ሢወራ የሤት እህቶቻችን ተሣትፎ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንደሚያሥፈልህ ከላይ የተጠቀሠው የአንባገነንነት መንሥኤም ሥብሠባው ጺም ለጺም (ወንድ ለወንድ)በመሆኑ ምክንያት ሣይሆን እንዳልቀረ የጉባኤው ተሣታፊዎች ገልጸዋል..


ቀደም ሢል ድርጅቱን ክደው ዛሬ ማሪኝ ሀገሬ ብለው የተመለሡት የድርጅቱ መሥራች አቶ Zewdalem Tadesse "ያለሤቶች ተሣትፎ ትግላችንና አብዮቱ ግቡን አይመታም"በማለት በታላቅ ወኔና ድምጽ የግራ እጃቸውን ቡጢ ሽቅብ ወደ ሠማይ እያወናጨፉ ሢናገሩ ሌላኛው ጉምቱ መሥራች አቶ Eyob Mihreteab Yohannes "ያለ ሤት እንኩዋን አብዬቱ አይነጋም ለሊቱ"በማለት ጉዋዲት Ma Hiን በቆረጣ ሢሾፉ ታይተዋል..ጉባኤውን ዘግይተው የተቀላቀሉት የድርጅቱ የሥነ ተዋልዶና የጅንጀና ምክትል ሀላፊና የክላሥተር አሥተባባሪ አቶ Leoul Zewelde የሤት አባላት ምልመላን በተመለከተ የተሠጣቸውን ሀላፊነት ያለ አበል ደከመኝ ሠለቸኝ ሣይሉ ለመሥራት ፍቃደኛ እንደሆኑ ገልጸው ለሥራ ማሥኬጃ የድርጅቱን አሮጌ ኦፔል መኪና ከሊቀ መንበሩ ጋር በፈረቃ እንዲጠቀሙ መሬት ተንበርክከው ለምነው ተፈቅዶላቸዋል..



ትግሉን በውጭ ሀገር የሚያሣልጡት የውጭ ጉዳይ ሀላፊዎች ወንድዬ አማናምና Kiram Kebede በበኩላቸው ቺኮችን "ዳያሥፖራ ነኝ" በማለት ወደ ድርጅቱ ለማምጣት እንደሚችሉ ከንፈራቸውን በምላሣቸው በቄንጥ ላሥሥሥ እያደረጉ አሣውቀው የጉባኤው መደምደሚያ ሆኑዋል።
ሸነግ የሠፊው ህዝብ ነው!!!


ሤት እህቶቻችን የሸነግ አይንና ዳሌ ናቸው!!!
ያለ ሤቶች ተሣትፎ የሸነግ አብዮት ግቡን አይመታም!!!!
ያለቺክ እንኩዋን አብዬቱ አይነጋም ለሊቱ.


!!!


ሸነግ ያብባል ይለመልማል!!


ሸነግ ይቅደም!!


ሸነግ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ!!!!


No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”