Saturday, April 22, 2017

ሸነግ ይጸዳል!

(Eyob Mihreteab Yohannes)

-

የፍየል ወጠጤ ልቡ ያበጠበት
እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበት
የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች
እነሱም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች
. . . ብዬ የሸነግ አመራር አባሌን ማንጓጠጤ የቅርብ ጊዜ ክስተት መሆኑ አይዘነጋም፡፡



-

እናም ጓድ ኪራም ከበደ፡
ጌታዬ፤ አለቃዬ፤ ጌታዬ፤ ሁለመናዬ፤ መላዬ መላዬ፤ ማኛዬ፤ ጸዴዬ፡፡
አንተ አብሮ አደጌ ላይ ክፉ እናገር ዘንድ ሼጣን፣ ሰኢድ እና ሻዕቢያዊ እብሪተኛ ባህሪዬ እኔን ማሳሳታቸው አሌ የማይባል ሐቅ ቢሆንም፣ አንተን ውድ ጓዴን በሕዝቡ ፊት በመናገሬ ከስህተተኛነት እንደማያድነኝ አሌ የማይባል ሃቅ ለመሆኑ በራሱ አሌ አይባልም፡፡

-
በዚህም ምክኒያት ከሸነግ ሊቀመንበርነት ስልጣኔን የምለቅቅ መሆኔን እየገለጽኩ በምትኬም ጓድ ዘውዳለም ታደሰን እና ጓድ ቢኒያም ሃብታሙን በእጩነት ሳቀርብ በታላቅ አክብሮት ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ጓዶች በብስለታቸው፣ በእውቀታቸውና በተፈተነ የአመራር ክህሎታቸው የተመሰከረላቸው ብልህ አመራሮቻችን ናቸው፡፡

-
የተከበረው ኮሚቴ እኔን ተክተውኝ ሸነግን እና ሸገራውያንን እንዲያገለግሉ በድምጽ ብልጫ እንዲመርጣቸው በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
-
እኔም ከአሁን በሁዋላ ሸነግ በመደበልኝ የፕሮፓጋንዳ እና ጥናት እና ምርምር ክፍል ውስጥ በፍፁም ቀናነት የማገለግል መሆኑን እገልፃለሁ፡፡
-
ሸነግ ይጸዳል!
-
-
-
ባላገር አይነፋም፡፡ ቢነፋም በደንብ አይነፋም!!
(የማይነበብ ፊርማ)

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”