Friday, April 21, 2017

ታላቅ ዜና

ታላቅ ዜና ለስፖርት አፍቃሪ እንዲሁም አዲስ አጀንዳ ናፋቂ ሸነጋውያን…
-
ሸነግ የነቄዎች ግንባር ነው።
ነቄዎች ደግሞ ከሰገጤ እሰጥ አገባ ቶፒኮች የፀዱ ፍተላዎችና ሙድ መያዞች በዘለለ… የሽቀላ ንፋስ አመጣሽ አጀንዳዎችን፣ ማለትም… እናት አገሬ፣ ብሄሬ፣ ሐይማኖቴ፣ እቴቴ… ወሬዎች የፀዳ ስብስብ ነው።

የሰሞኑን የፌስ ቡክ ፀዴ ሙድ መያዣ አጀንዳ እጥረት ከግምት ውስጥ በመክተት… የሸነግ ግብር ሀሌታው ሀ ግብር ከፋይ ከፍተኛ ባለሃብት አባሎች የሚሳተፉበት… ፀዴ የእግር ኳስ ቡድን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ላይ ነን።

ይሄ አውሮፓ ላይ የምትሰሙት፣ ቻይና ሳትቀር የገባችበትን በምናምን ነጥብ ተጫዋች የመግዛትና የማዘዋወር ዜና በሸነግ ክለብ ልንተገብረው ነው።
ወድ ሸነጋውያን… የሸነግ ድሪም ቲማችሁን ወዲህ በሉ እስኪ?
ጉዳዩ ሲሪየስ ነው።
ጉዳዩ ሽቀላ ነው።

ከአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮን ሺፕ በዘለለ… ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ… በተጋባዥነትም ቢሆን የሚወከል ቲም ልናቋቁም ነው። እግር ኳስን ከፍ ልናደርገው ነው።
ጉዳዩ ሲሪየስ ነው።
ሸነግ አይቀልድም።
ቢቀልድም ሙድ ለመያዝ ነው።

ጀለስካ ኪራም ይህን ዜና አብስርልኝ እንዳለኝ፣ ጠርናፊያችን እየባ እንሸቅልበት ብሎ ምፅ! ምፅ! እንዳለኝ እኔ ብንያም እንደፃፍኩላችሁ።

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”