Friday, April 21, 2017

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ


በአነግ (የአራዳ ልጆች ነጻ አውጪ ግንባር) የታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

-

ዲር ጀለስካ ተንቀናል፣ተዋርደናል ብታምንም ባታምንም በቁማችን ሞተናል!
-

እኛ ሰው ባደረግናት ከተማ ጎሩጊሮጋራጌሪ ከሚባል ፓስፊክ ኦሺን በግራ ታጥፎ ካለ ሰፈር የመጣ ሰገጤ ጢባ ጢቢ ……. አንዴ እደግመዋለሁ ጢባ ጢቢ ….. ሲጫወትባት አይተን እንዳላየ እስከመቼ!

-

አረ ፕሊስ ካቻ ዊ አር ቤተር ዛን ዛት! የአራዳ ልጆች ከተሞችን (ናዝሬት፣ደብረዘይት፣አዱ ገነት …..) ከሰገጤ ወረራ መከላከል የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል! እርግጥ ነው እኛ ለሰገጤዎች ህንዳቸው ነን! ሆኖም የተናቀ ቁ* ያስረግዛል እንዲሉ በአናታችን ላይ ከህንጣ ላይ ህንጣ፣ከሎሪ ላይ ሎሪ፣ከቺክ ላይ ቺክ፣ከአቡ ሚስማር ላይ ኮሎምቢያ ሲደርቡ እኛ የበይ ተመልካች ሆንን እኮ!

-

ስለዚህም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቆይ የአራዳ ልጆች እንዴት አድርገን የፖለቲካና ኢኮኖሞ ሜይን ስትሪም መሆን እንደምንችል መምከሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀናል!

-

አዋጁን ለማስፈጸም በኡሩጉዱሩው ላቦሮ Eyob የሚመራ ኮማንድ ፖስት ያቋቋምን ሲሆን ከኮማንዱ ፖስቱ እውቅና ውጪ ከሰገጤ ጋር ማሽካካት፣ግንኙነት መፍጠር (ግብረስጋ ግንኙነትን ጨምሮ)፣ ወ.ዘ.ተ. በጥብቅ እንደተከለከለ እናስታውቃለን!

ግልባጭ …. በሃይለማሪያም ለሚመራው የሰገጤ ኮማንድ ፖስት! (እና እናንተ ብቻ ናቹ ኮማንድ ፖስት ያላቹ ያለው ማን ነው)

#ሰገጤ#ሸነግ#የአራዳልጆችነጻአውጪግንባር(አነግ)

#አነግኮማንድፖስት

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”