Friday, April 21, 2017

የሸነግ አሥርቱ ትዕዛዛት

ከወንበዴው እዮብ ምህረተአብ

( የሸነግ አሥርቱ ትዕዛዛት)
* * * * *
(1)
ሸነጋዊነት ማለት ስልጡን ማንነት፣ የከተሜያዊ ስብዕና ባለቤት መሆን ማለት ነው፡፡ ከ Regional Boundary ጋራ ንኪኪ የለውም፡፡ እንኳንስ አዲስ አበባ ተወልደህ፣ ኒውዮርክም እየኖርክ ሰገጤነት ላይፋታህ ይችላል፡፡
ሸነጋዊነትን በወንዜ ልጅ መለኪያ መመዘን በራሱ ሰገጤነት ነው፡፡
(2)
ሸነግ የዘር መጠላላትን፣ ማንጓጠጥን፣ መፈራረጅን አጥብቆ ይጠየፋል፡፡ ሰገጤነት አስተሳሰብህ እንጂ ዝርያህ አይደለምና፡፡
(3)
ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ እኩል ናት፣ ወይንም ሴት ልጅ ከወንድ እኩል እድል ሊሰጣት ይገባል የሚለው አስተምህሮ ሊሰጥ የሚገባው ለሳቬጅ ሰገጤ እና ለሪታርድድ እንጂ ለሸነጋውያን አይደለም፡፡ ምክኒያቱም የሴት እኩል መሆን የኖርንበት፣ የምንኖርለት ጥሬ ሃቅ እንጂ ምጽዋት/ደግነት ስላልሆነ፡፡
(4)
ሸነግ አይደለም እኛ አገር ያሉ ሃይማኖቶችን፤ ኢ አማኒነትን፣ፓጋንነትን፣ እንዲሁም ገና ወደፊት የሚመጡ/የሚፈጠሩ እምነቶችን እና አተያዮችን በህግም በምግባርም ያከብራል-ያስከብራል፡፡
(5)
ሸነግ አሁን ያለው ገዢው ፓርቲ ሰገጤ እና የሰገጤዎች ስብስብ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ነገር ግን ሊገዙ የቋመጡ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና እንገንጠል የሚሉ ቡድኖችም እኩል ሰገጤዎች እና እድል ቢሰጣቸው ከገዢው ፓርቲ ያላነሰ ሰገጤ አስተዳዳሪ ይሆናሉ ብሎ ያምናል፡፡
በዚህም ሸነግ ከየትኛውም የፖለቲካ ስብስብ ጋራ ንኪኪ የለውም፡፡ አይኖረውምም፡፡
(6)
ሸነግ በማህበራዊ ለውጥ (Social Evolution) እንጂ በነውጠኛ አብዮት (Militant Revolution) ፈጽሞ አያምንም፡፡ ይሄ የሆነው በሃይል የሚመጣ ለውጥ አገር ሲበጅና ሲጠቅም ያልታየ ጥሬ ሃቅ ስለሆ ነው፡፡
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
(አንባቢ ሆይ፣ ጠንቅቀህ እንደምታውቀኝ ሕግ እና ምክር አልወድም! አባቴ የመከረኝን ተግብሬ አልጨረስኩም፡፡እናም አስርቱን ትዕዛዛት ጽፎ መጨረስ አቃተኝ፡፡ አንተው ጨርሰው!! እኔ ግን ቅጣዩን ልቀደድልህ!)
-
-
(7)
የሸነግ መስራች፣ ጠንሳሽ፣ መሪ፣ ሊቀመንበር፣ የጦር ኢታማዦር ሹም፣ ገንዘብ ያዥ፣ የመሬት አስተዳደር፣ የኢንቨስትመንት ክፍል ሃላፊ፣ . . . የፓርቲው ማህተም ባሉካ ጠቅላይ ሚኒስቴር እኔ ነኝ!
(8)
አቅም፣ ሃብት እና ንብረቱ ሲተመን ከአንድ ሚልዮን ብር ያነሰ በሙሉ ሰገጤ ነው! ከሌለህ የለህም፡፡ የለህማ!!
down down ችጋራም!
down down ቀንጫራ!
(9)
ሰገጤው በሙሉ በጎሳ ተጠርንፎ ስለሰከረ፣ ሸነግ የኢትዮጵያዊነት ሰጪና ነሺ ነው፡፡ የዚህ የስራ ሂደት መሪውም እኔና እኔ ነኝ!!
(ጉቦ is most welcome!)
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
-
(10)
(በመጨረሻም)
እያወቅክ አትናደድ፡፡ ሶስት ቀን ለመኖር አራት ቀን አትበሳጭ፡፡ አሪፉ ነገርህ ከድክመቶችህ በእጥፍ ይልቃል፡፡ አንተ Unique ፍጥረት ነህ፡፡ ከነንፍጡ፣ አንተ ፀዴ ሰው ነህ፡፡ አንተነትህን (ያንን crazy ድብቅ ሁለተኛው አንተነትህን ጨምሮ ) ውደደው፣ አዋራው፣ አክብረው፣ እውቀት/መረጃ ስጠው፡፡ ብቸኛው ሃብትህ ሰው ነው፡፡ አሪፍ ሰዎችህን loyal ሆነህ እና ተንከባክበህ ያዛቸው፡፡ (እኔንም ከነ አመሌ ያዘኝ፣ ስበጠብጥ ባላየ እለፈኝ! lol)
-
-
መልካም ገና፤ መልካም በዓል አለቃዬ! ጌታዬ! ማኛዬ!!፥
-

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”