About Us

                    (ስለ ሸነግ፣ በግርድፉ፡፡)

                          * * * * *
(1)

 ሸነጋዊነት ማለት ስልጡን ማንነት፣ የከተሜያዊ ስብዕና ባለቤት መሆን ማለት ነው፡፡ ከ Regional Boundary ጋራ ንኪኪ የለውም፡፡ እንኳንስ አዲስ አበባ ተወልደህ፣ ኒውዮርክም እየኖርክ ሰገጤነት ላይፋታህ ይችላል፡፡  ሸነጋዊነት በወንዜ ልጅ መለኪያ መመዘን በራሱ ሰገጤነት ነው፡፡

(2)

 ሸነግ የዘር መጠላላትን፣ ማንጓጠጥን፣ መፈራረጅን አጥብቆ ይጠየፋል፡፡ ሰገጤነት አስተሳሰብህ እንጂ ዝርያህ አይደለምና፡፡

(3)

ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ እኩል ናት፣ ወይንም ሴት ልጅ ከወንድ እኩል እድል ሊሰጣት ይገባል የሚለው አስተምህሮ ሊሰጥ የሚገባው ለሳቬጅ ሰገጤ እና ለሪታርድድ እንጂ ለሸነጋውያን አይደለም፡፡ ምክኒያቱም የሴት እኩል መሆን የኖርንበት፣ የምንኖርለት ጥሬ ሃቅ እንጂ ምጽዋት/ደግነት ስላልሆነ፡፡

(4)

ሸነግ አይደለም እኛ አገር ያሉ ሃይማኖቶችን፤ ኢ አማኒነትን፣ፓጋንነትን፣ እንዲሁም ገና ወደፊት የሚመጡ/የሚፈጠሩ እምነቶችን እና አተያዮችን በህግም በምግባርም ያከብራል ያስከብራል፡፡

(5)

ሸነግ አሁን ያለው ገዢው ፓርቲ ሰገጤ እና የሰገጤዎች ስብስብ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ነገርግን ሊገዙ የቋመጡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና እንገንጠል የሚሉ ቡድኖችም እኩል ሰገጤዎች እና እድል ቢሰጣቸው ከገዢው ፓርቲ ያላነሰ ሰገጤ አስተዳዳሪ ይሆናሉ ብሎ ያምናል፡፡

በዚህም ሸነግ ከየትኛውም የፖለቲካ ስብስብ ጋራ ንኪኪ የለውም፡፡ አይኖረውምም፡፡

(6)

ሸነግ በማህበራዊ ለውጥ (Social Evolution) እንጂ  በነውጠኛ አብዮት (Militant Revolution) ፈጽሞ አያምንም፡፡ ይሄ የሆነው በሃይል የሚመጣ ለውጥ አገር ሲበጅና ሲጠቅም ያልታየ ጥሬ ሃቅ ስለሆ ነው፡፡

-

(ይኸው ነው)





Web Design : Dogali Entertainiment (Alula Getahun)
Email : alu2get@gmail.com

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”