Friday, April 21, 2017

ሸነጋውያን

(Michael Gebre)
* * * * *
ሸገር ማለት የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሞዴል ናት ፣ ከየትም ና ከየትም ሸገር የምታከብርህ በስራህ ና በአመለካከትህ እንጂ በማንነትህ አይደለም።
ሸነግ ደግሞ ይህንን የሸገር metropolitan ideology በሰገጤ አtመለካከት የበላይነት እንዳይሸነፍ ነፍጥ ሳይሆን mocking ን እንደ መሳርያ አንግባ የምትከላከል think tank ናት።
-
ሸነጋውያን በአስተሳሰብ/በአመለካከት፣ በፓለቲካ ፣ በእምነት ፣ እና በሁሉም ልዩነት ያምናሉ።።
በ ልዩነት ውስጥ አንድ መሆንን፤ በልዩነት ውስጥ አብሮ ለአንድ አላማ መስራትን ይችሉበታል።
ሸነጋዊ ሰጥቶ መቀበልን ያቅበታል ጭዌው፣ ቢዝነሱ ፣ ፖለቲካው ሳይቀር Compromising ነው።
-
ሸነጋውያን have character, integrity, unselfishness, understanding,conviction, loyalty and respect!
-
(ጀለሶች ተረጋጉ አትሳሳቱ!)
-
ሸነጋዊ ማለት የ ሸገር ልጅ ማለት አይደለም፣ ሸገር ስንት ሰገጤ በሆዷ ይዛለች። ሰገጤ ማለትም የ ገጠር ልጅ ማለት አይደለም ....ስንት የለየለት የጨሰ አራዳ/ሸነጋዊ በየገጠሩ አለ ?...
-
ሸነጋዊ ideal Character ነው;
ሸነጋዊነት በአብዛኛው ሀበሻ/ ኢትዮጽያዊ ልብ ውስጥ የተሰነቀረ ገፀ ባህሪ ነው .. እንደ Superman በሆንኩኝ ብለው የሚጔጉለት icon ነው ... መሪዎቼ እንደ ጋንዲ/ማንዴላ/ በሆኑልኝ ብሎ የሚያልመው ህልም ነው። ሸነጋዊነት !!
-
ሸነጋዊነት
የ አዎንታዊነት / positivity/​ መንፈስ ነው ፤
የ በጎነት ዝናም ፤
የ አንድነት ና አብሮነት መብረቅ፤
የ ይቅርታ ና የ ተሸናፊነት ደመና ፤
የ ፍቅር አውሎ ንፋስ ነው !!!!
(ይህ ንፋስ ....)
ከየትም አቅጣጫ/ ከኦሮሞ ይንፈስ ከትግራይ ፤ ከ አማራ ይንፈስ ከደቡብ ፤...................፤......፤ ከ ጨርቆስ ይምጣ ከ ቦሌ/....
በቃ ሸነጋዊነት ነው።
ሸገር ደግሞ የዚህ ሁላ የ ፍቅር፥የአብሮነት፥የበጎነት መአዛ ማብላያ ! የ ስኬት ና ዘመናዊነት መጋዘን ! የሊቁ ና መሪው መሰባሰቢያ ! ናት።
ኢትዮጵያ የሚጣፍጥ የ/ትልቅ ድስት ቀይወጥ ብትሆን ሸገር ደግሞ እፍታው ናት!
-

(እኛ ሰገጤ የምንለው...)
-
ከኔ ውጭ ላሳር የሚለውን ነው፤ ፍቅር ሳይሆን ጥላቻ የገዛውን ነው ፤ የኔ ብሄር የበላይ የሚለውን ነው፤ እርቅን ሳይሆን ሁሌ በደልን የሚሰብክውን ነው፤ መደጋግፍን ሳይሆን መጠላልፍ የሚያቅደውን ነው፤
አስመሳይ፣ ተንኮለኛ፣ ሸረኛ፣መተተኛ፤ በቀለኛውን ነው።
-
ሰገጤዝም አክራሪነት ነው፣ ዘረኝነት፣ ጠቅላይነት ነው፣ Egoism ፣trumpism ነው።
-
በሸነግ መመዘኛ መሰረት ብዛት ያለውን ሰገጤ ና ጠሽ ሰዎችን በማምረት የ ድያስፖራ ኮሚኒቲ የሚደርስበት አልተገኘም።
ይህም የሚያሳየው ስግጥና የሚገኘው በትውልድ ወይም በአካባቢ ሳይሆን ከጠሽ ሰው ወደ መንጋ ጠሽ ሰዎች በሚተላልፍ ትውልድ/አገር ገዳይ በሽታ ነው።
ሰገጤ ባለሀብት ሰራተኛ የሚቀጥርበት መመዘኛ ዝምድና፣ጎጥ ና ብሄር ነው እናማ በትምህርቱ ጥሩ ውጤት ያለው በፈጠራ ችሎታው ድርጅቱን/ባለሀብቱን ና አገሩን እንዳይጠቅም ተግዳሮት ይሆናል ።
ሰገጤ የኢህአዴግ ፖለቲከኛ ; በሚመራው የፌደራል መስርያቤት ውስጥ በብቃት ሳይሆን በብሄር ወይም በአካባቢ የሚቀርቡትን ሰዎች ይሰገስግና ለህዝብ ሮሮ መንስኤ ለ ፓለቲካ ስርአቱ አደጋ ይሆናል።
ሰገጤ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ስለ ኔልሰን ማንዴላ ቢያነብም /ቢያወራም ስለ ጥላቻ ግን ይዘምራል ።
ሰገጤ ባለስልጣን ስግብግብ ነው፣ ሲሰርቅ እንኴ አውሬ ነው ፣ በትንሽ ጥቅም አገር ይሸጣል፣ (የመስረቅ ትንሽ የለውም ቢባልም ቅሉ ) ( አለው እንጅ ስንት ፀዳ ያለ smart ሸነጋዊ ሌባ አለ )
ሰገጤ የፖለቲካ አክቲቪስት;- ፍቅርን ሳይሆን ጥላቻን ፣
ይቅርታን ሳይሆን በቀልን ፣ አንድነትን ሳይሆን መነጠልን ፣ ውጤትን ሳይሆን ውድቀትን ፣ መከባበርን ሳይሆን መናናቅን ፣አዎንታዊ አመለካከት ን ሳይሆን አሉታዊ አመለካከትን ይሰብካል።
ሰገጤ ምሁር ታሪክን አጣሞ ያስተምራል፤ ምጡቅነቱን ለህዝብ ባለው ንቀት ለማስመስከር ይዳዳል፤የመፅሀፉ ርዕስ "የስኬት ሚስጥሮች" ሳይሆን " የውድቀት ስትራቴጂዎች" አይነት ናቸው !
ሰገጤ የደጋፊ ና የተቃዋሚ መንጋ ; - አይነስውር ነው፤ ማመዛኛውን አስቦክሞ ሆ እያለ መሪውን ገደል ይከታል።
ዲሞክራሲ፣ ነፃነት እያል ይጮሀል ነገር ግን የለየለት የ የአምባገነን ማ/ሰብ Cell ነው። የፍቅር ና የ ሀሳብ ድኩማኖችን ፤የጥላቻ ና Self-centered አምባገነኖችን አንግሶ ..........ተራማጅና አስተዋዮችን ፤ Democrat ና ሞጋቾችን ያረክሳል።
-
በሸነግ እምነት; ኢህአዴግ የለየለት የሰገጤ ፓርቲ ነው አብዛኛው ተቃዋሚ ነን ባዮችም ያው ክው ያሉ ዥልጥ ሰገጤዎች ናቸው።
ለ ሸነጋውያን የሚመጥን የፖለቲከኞች ስብስብ ገና አልተፈጠረም።
-
(ግን ተስፋ አለ!)
-
በየቤቱ ስንት ማንዴላ አለ ? ስንት ስንት Dalai lama አለ ? ስንት Malala Yousafzai አለ? ስንት ነጋሶ ጊዳዳ ስንት ልደቱ አያሌው፤ ስንት መለስ ዜናዊ፤ ስንት መስፍን ወ/ማርያም፤ ኸረ ስንት የ ነፃነት የ ፍቅር እና የአንድነት ችግኝ አለ ?
(NB -ከላይ የተጠቀሱት መላዕክት አይደሉም እስከ ነ ችግሮቻቸው ለምሳሌ የቀረቡ ሰዎች ናቸው 😊)
የ ሰገጤ መንግስት ስርአት ፤ የ ሰገጤ ተቃዋሚ ሽኩቻ፤ የ ሰገጤ መንጋ ጋጋታ ......የፈጠረው ርኩስ መንፈስ ግን ከዛፎቹ አልፎ እነዛን ችግኞች ወደ አደባባይ ወጥተው እንዳያብቡ በያሉበት ያጠወልጋል።
-
እናማ ማን ሸነጋዊ መሆን የማይፈልግ አለ?
ማን በስግጥና ያልመረርው አለ ?
እናማ ዛሬዉኑ ሸነግን ተቀላቀልና ዛፎቹ ቀርተው ችግኞቹ እንዳይጠወልጉ የሸነጋዊነት ኃላፊነትህን ተወጣ።
-
ስግጥናን እናውግዝ !
Let's Mock ስግጥና
-

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”