Friday, April 21, 2017

የሸነግ የአቋም መግለጫ

(ባለ 10 ነጥብ የሸነግ የአቋም መግለጫ)
* * * * *
(1)
ሰገጤ ሰው የሴትን ቂንጥር ይተለትላል፣ ይቆርጣል፡፡ የሴትን ብልት ሶሉ እንደተገነጠለ ጫማ ይሰፋል፡፡
(2)
ሰገጤ ሴትን ይደፍራል፣ ይጠልፋል፡፡ ይደበድባል፡፡ ያንጓጥጣል፡፡
(3)
ሰገጤ Flirting እና ስድብን አይለይም፡፡ ጅንጀናና ሃራስመንትን አይነጥልም፡፡
(4)
ሰገጤ እድል ተሰጥቶት ሲጀናጀን እና ሲላፋ እጁ የሴት ገላ ይልጣል፡፡ አንገት ይቆለምማል፡፡ እጇን ወለም እስኪላት ይጠመዝዛል፡፡
ከዛ ኻ!ኻ!ኻ!ኻ! እያለ ይገለፍጣል፡፡
(5)
ሰገጤ ሴትን ማድመጥ፣ ማዋራት፣ ማማከር፣ ትንሽም ትሁን ስጦታ መስጠት፣ ማሳቅ፣ ማጫወት፣ መንከባከብ፣ ማሳቅ የተባሉ ችሎታዎች ዘረ መሉ ውስጥ የሉም፡፡
(6)
ሰገጤ ፍቅር ሲሰራ selfish ነው፡፡ ለሴቷ ስሜት አያስብም፡፡
(7)
ሰገጤ በጥፍራቸው ጥረው ግረው ኑሯቸውን ያቸነፉ፣ empowered የሆኑ ሴቶች ለትዳርና ላገር ጠቃሚ ናቸው ብሎ ስለማያምን፣ ሰርክ ኮምፕ እንደሸከሸከው ኖሮ ኖሮ ይሞታል፡፡
(8)
ሰገጤ ጭፍን ዘረኛ ስለሆነ ከሱ ብሄር ውጪ የሚገኙ ምርጥ ሴቶችን የማግባት ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ ካገባትም የዘር ጆከር እየመዘዘ አዛ ሲያደርጋት ይኖራል፡፡
(9)
ሰገጤ stuck ያደረገ ዱልዱም ነው፡፡ የቤት ውስጥ ማስተዳደርና ልጆች ማሳደግ ላይ ሚስቱን ማገዝ ክብረ ነክ ድርጊት አድርጎ ያስበዋል፡፡
(10)
ሰገጤ የማይሸጥ የማይለወጥ ዥልጥ ዙንጆሮ ስለሆነ እያንዳንዷ ሸነጋዊት ሴት ከሰገጤ ራሷን እንድትጠብቅ ሸነግ የምክር፣ የህግ፣ እንዳስፈላጊነቱ የሃይል እርምጃን ትወስዳለች፡፡
-
ሴትን አለማክበር ሰገጤነት ነው፡፡ አራት ነጥብ!
-
-
ሴት ልጅ ከከንፈር መጠጣ፣ ከብስጩ ጽንፈኛ ፌሚኒስቶች ልፈፋና ከNGO ጆካ ፈለጣ ተኮር እትት ግትት በላይ ናት፡፡
-
-
-
-
እንኳን ለተከበረው March 8 አደረሰን፡፡
ኪራም ከበደ
የሸነግ ሊቀመንበር
(የማይነበብ ፊርማ)

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”