Friday, April 21, 2017

የሸ.ነ.ግ Business Trend Analysis Report

(ወቅታዊ የሸ.ነ.ግ Business Trend Analysis Report)
* * * * *
ገተታ በሌለው፣ በወደ ገደለው አነጋገር፡
ፊንፊኔ የኦሮሚያ መቀመጫ ከሆነች አይቀር፣ ድሪባ ኩማ የሸገር ከንቲባ ከሆነ አይቀር፣ ፊንፊኔ ዙሪያ ወደፊት መሬት ገዝተን ቤት ሰርተን ልጅ የምናሳድግበት ብቸኛው የማርያም መንገዳችን ከሆነ አይቀር (ምፅ!) (ምፅ!)
-
ብሄር አልባውና እጅግ ጸዴው፣ እግዜር እጁን ታጥቦ የሰራው የአዲስ አበባ ልጅ ከኦሮሞ Economic Revolution የድርሻውን ሊያገኝ ይገባል፡፡
-
-
-
እርግጥ ነው፣ ሸነግ የኦሮሞ Economic Revolutionንን ተከትሎ፡
-
የትግሬ 22 እና ሰሚት ላይ Evolution፡፡
.
የአማራ Militant Identity Creation፡፡
.
የሱማሌ በርጫ ምርቃናይዜሽን፡፡
.
የሲዳማ ክልል እንሁናይዜሽን፡፡
.
የስልጤ Forgery Tripleization፡፡
.
የአደሬ GDP Millionaireization፡፡
.
የኢህአዴግ አዲስ የኢትዮጵያዊነት Confused Exploration፡፡
-
ትረንዲንግ መፈጠሩ የማይቀር መሆኑን ቀድማ ተንብያ፣ የጥናቷ Conclusion ላይ Lol እና (ምፅ!) የሚሉ ቃላትን ተጠቅማ ብትደመድምም፤ የኦሮሞ ኢኮኖሚክ ሪቮሊዩሽን እትት ግትትን አስታክኮ ፈሰስ ከሚደረገው የቢልዮን ብሮች ፍሉስ ላይ እያንዳንዱ ዘር አልባ ሸነጋዊ ከእናት አገሩ የድርሻውን Pick ማድረግ እንዳለበት ሳይታለም የተፈታ እውነት ነው፡፡
-
-
-
ስለዚህም በዚህ በኦሮሞ Economic Revolution የቢልዮን ብሮች ካርታ ላይ ሸነግ ምፅ! ምፅ! እያለች፤ የኦሮሞ ሸነጋውያንን ዝምድና ታክካና አስታክካ በPost ፈሰሱ ኢንቨስትመንቶች ዙርያ Consult ለማድረግ፣ የStock Dealer አገልግሎትን የመስጠት፣ ለመደራደር፣ ለመተጋገዝ፣ ለመተባበር፣ ለመረዳዳት ዝግጁ ናት፡፡
- - - -
(በቀላል አማርኛ)
እኛ ሸነጎች Pragmatic Jew ነን፡፡ መንግስት ሲጨናቆርና ቅጥ አምባሩ ሲጠፋው ከሚለቀው ቻፓ ላይ የድርሻችንን ለመቁረስ ብቃቱም፣ ወኔውም፣ ፍጥነቱም፣ ጭንቅላቱም፣ ድፍረቱም አለን፡፡ እንኳንስ ከቢልዮኖች ፈንድ፣ ከኮማንድ ፖስት ክፍተትምም ከመጠቀም አልተመለስንም፡፡
(በወረደ ቋንቋ)
ይሄ የአገሪቱ The 1% ክሬም ስብስብ የሆነው የሸነግ Think Thank Group አባላት ለኦሮሚያ እጅግ ጠቃሚ ቀኝ እጆች ናቸው፡፡ ኦሮሚያ ደግሞ የሸነግ ቀዳሚዋ ወላጅ (ምፅ!) በሞጋሳ አጥማቂ (ምፅ!) ብቸኛ ተዋሳኝ ጎረቤት (ምፅ!) እናት (ምፅ!) (ምፅ!) (ምፅ!) ናት፡፡
-
-
(ጌታዬ!)
-
ኦሮሚያና ሸነግ ጋብቻቸው እንደ ካቶሊክ ጋብቻ ነው - ፍቺ የለውም!
(Galatooma)

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”