Thursday, April 20, 2017

በትልቁ መጥበብ

በትልቁ መጥበብ

(ቢኒያም ሐብታሙ)

በሁሉም ረገድ ትክክል የሆነ፣ ለአንድ ህብረተሰብ ዘለቄታዊ የፖለቲካ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናና ልማትን የሚያጎናፅፍ theory(ፅንሰ ሃሳብ) የለም።
አለማችን በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ Grand የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ እሳቤዎችን አስተናግዳለች።
እነዚህ Grand theories... በወቅታቸው እንደ ሃይማኖት ተሰብከው በግለሰብ ደረጃ መስዋትነትን አስከፍለው አልፈዋል።
ፊውዳሊዝም፣ ማርክሲዝም፣ ሶሻሊዝም፣ ኮሚዩኒዝም፣ አይድያሊዝም፣ ሊበራሊዝም፣ ሁሉም እሳቤዎች በወቅታቸው ትክክል ሆነው አልፈዋል። ርዝራዣቸው ግን እስከ ዛሬ ድረስ ቅርፁን እየቀያየረ ቀጠሏል።
አሁን… ከሞላ ጎደል፣ በአብዛኞቹ የአለም አገራት ጊዜው የኒዮ ሊበራል ዲሞክራሲን መንገድ እየያዘ ይመስላል። እሱም የጊዜና ሁኔታ ጉዳይ እንጂ መቀየሩ አይቀርም።
የሰው ልጅ የኑሮና የእድገት ደረጃ እየተለወጠ በመጣ ቁጥር፣ ኑሮውን የሚመራበት የፖለቲካ፣ኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት ፅንሰ ሃሳብ አብሮ ይለወጣል። Nothing stays as it is.

አዎ! 

ይህን የአለምን ተለዋዋጭ ሁኔታ ስታጤን፣ አንድ ነገር ላይ ድርቅ አትልም። status quo always changes.
ዘመናዊ እሳቤ ማለት ደግሞ፣ ታሪክንና ማንነትን ሳይዘነጉ ላለህበት ጊዜ ኋላ ቀር የሆኑ እሳቤዎችን መቀየር ነው።
እንደ አገር፣ አሁን ላይ የብሔር ብሔረሰብን እኩልነት የምትሰብክበት ዘመን አይደለም። እሱን ተወውና፣ የሰው ልጆችን እኩልነት ሁሉ የምትሰብክበት ጊዜም አይደለም። አሁን ላይ አብዛኛው ህብረተሰብ ከሱ እውቀት ደረጃ በላይ ነው። …በተለይ ደግሞ፣ 'ተምሯል' የምትለው።
ይሄ ዘመን ስለ እገሌ ፓርቲ፣ ወይም እከሌ ስለሚባል ተቀናቃኝ አልያም ተቃዋሚ የምታወራበት ጊዜ አይደለም።
አሁን ጊዜው፣ የጋራ የሆነን ነገር የማሰቢያ ጊዜ ነው።

ይሄን ተራ የቲፎዞነትና የፖለቲካ ሃይማኖትህን ወዲያ አሽንቀንጥረህ ጥለህ ከጠበብክበት እሳቤ ውጣ!
አስተሳሰብህን አስፋ!

ቢያንስ ብሔርን ዝለለውና አንድ እርከን ወደ ፊት ተራመድ!
ካልበጠስከው በቀር ሺ ብታከረው፣ ብሔር ከአገር አይሰፋም።
ይሄን ጠባብ ስብከት ለፖለቲከኞች ተወው።
የትም አለም ብትኖር፣ ሰው ቀድሞ የሚጠይቅህ አገርህን ብቻ ነው።
ከዛ የጠበበ ፍላጎት ማንም የለውም።

ስለዚህ ወዳጄ… 
ከጠበብክ አይቀር በትልቁ ጥበብ!
"አገር አለኝ" በል!

በል።

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”