Sunday, April 23, 2017

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ - (አዱኛ ሌሊሳ)


(By: Adugna Lelisa Sime)

* * * * *

ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከተ አጭር መግለጫ
ሚያዝያ 14 ቀን 2009ዓም
.
በቅርቡ አንዳንድ የአገራችን ክልሎች(በተለይም የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች) የአገሪቱን ህገ መንግሥት ባልተጣረሰ መልኩ ኢኮኖሚያቸውን ለመገንባት፣አቅማቸውን ለማሳደግ እና የህዝቦቻቸውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወኑ ያሉትን ተግባራት የሸነግ ስብስብ በትኩረት የሚመለከት እና  የሚደግፍ ቢሆንም ይህ አካሄድ በክልሎች መካከል አላስፈላጊ ፉክክር እንዳያመጣ እና አገራዊ አንድነቱን የበለጠ ስጋት ላይ የሚጥል እርምጃ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ  ከወዲሁ አበክረን ለማሳሰብ እንወዳለን።

.
የፌዴራል መንግስቱም የክልሎቹን በጎ አላማ ከማጣጣል ይልቅ ትልቁን ስእል በማየት እና በመረዳት ይህንን ተነሳሽነት ለመደገፍ እና አስፈላጊውን ትብብር ለመቸር  ጉዳዩን በአንክሮ እንዲያጤን እናሳስባለን።

*****

በመጨረሻም :—

ከሰሞኑ የግብፅ ጦር ኤርትራ ውስጥ ለመስፈር ማቀዱን በሚመለከት የተሰማውን ዘገባ ተከትሎ ሃሳብ የገባን የሸነግ ሸንጎ አባላት በኢትዮጵያ መንግሥት ድንበር አጠባበቅ የህዳሴ ግድቡንና ቁጥር ስፍር አልባ ህፃናትን ተሰርቀን የፌስቡክ አጀንዳ ሆነው ከመቅረታቸው በፊት መንግስት ግድቡም ሆነ ህፃናቱ በጊዜያዊነት ወደሸገር የሚጠጉበትን መላ እንዲፈልግ ልንመክር እንወዳለን። =D

ሸነግ!!(የሸገር ነፃ አውጭ ግንባር =D  )

በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን በማኅበራዊ ለውጥ እንታመናለን!!


No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”