Friday, April 21, 2017

ሃያትን የምወዳት . . .

Leoul Zewolde
-
(ሃያትን የምወዳት . . .)
* * * * *
.
ሃ ያ ት ን የምወዳት . . . እናቴ እስኪ እንደሷ ጭዋ ልጅ ሁን ብላ በነጋ በጠባ ምሳሌ ስለምታረጋት አይደለም ። ዱምቡሉ አይኖቿ ስለሚያምሩና ሳማቸው ሳማቸው ስለሚለኝ አይደለም ። እኛ ቤት ያለው ቲቪ እኮ የናንተን ቤት እስከጎረቤታቹ ነው 'ሚያክለው እያለች ስለምታበሽቀኝና ሳኮርፍ ስለምታባብለኝ አይደለም ። አንገቷ ላይ ጥቁር ነጥብ አይቼ ሃዩ እስላም ሆና እንዴት ማርያም ሳመቻት ? ብዬ ለብዙ ግዜ ብቻዬን ስለተወዛገብኩ አይደለም ። ከላይ ሰፈር ሱቅ ፊኛ ስንገዛ 24 ቁጥርን መርጣ ግብድዬ ቀይ ፊኛ ስለደረሳት አጃጅዬ ልሰርቃት አይደለም ። ያቺ አጭርዬ የቤት ሰራተኛቸው መኮሮኒ ቀርባ በሉ አንድ ላይ ብሉ ስትለን አይ እኔ < ሰው ቤት እንዳትበላ ተብያለው > ብዬ በራሷ በሃያትዬ እጅ ደስ እያለኝ ስለምጎርስ አይደለም ።

ኩኩሉ ስንጮት እተደበቅኩበት ድረስ መጥታ አንደኛ ካለቺኝ አጮልቃ አይታለች ብዬ በእፍርት ድጋሚ ስለማስቆጥራት አይደለም ። ስደበድባት አባቴ ፖሊስ ነው እና ደሞ ለልደቴ አልጠራህም ብላኝ ተለማምጬ እሺ አልናገርብህም ስላስባልኳት አይደለም ። ፀጉሯን የምታያይዘበት ፖኒተር ፣ ቡፍ የሚል ቀሚስ ፣ ከለር ፣ ቢጫ መነፅር ፣ ቲያራ ፣ የሚያበራ ጫማ ፣ ቋ' ቋ' ጫማ ፣ ብልጭልጩ ቦርሳ ፣ ሸዋሊያ ፣ ባርቢን ጨምሮ ነፍ አሻንጉሊት ከውጭ አገር ስለተላከላት አይደለም ። የኛ አላህ እና እግዛቤር ቢደባደቡ ኮ አላህ ያሸንፋል ብላ እምነቴን ስለምትሸረሽረው አይደለም ።
-
በማታ ከሩቅ ያለ አምፖል ስናይ አይናችንን እንደመጨፈን አርገን ብዥዥ ያለ ቀጭን መስመር እየሰራን ባረዘመ ስለምንጮት አይደለም ። ሮቤል ብዙ ግዜ አብሯት እየሆነ ስለሚያስቀናኝ አይደለም ( ሰፈር ባይቀይሩ ኖሮ ልፈነክተው ነበር ) ። ሸንኮራ ሻጭ አንጓ እንዲሰጠኝ እየተከተልኩ ስለምን አይታ ፊሽካ ያለው ኢሊፖፕ አስገዝታ ስላስመጠጠቺኝ አይደለም ። ሸለለ . . . ፑቱካ ተጣልቼሃለው ! ብላ ግቢያቸው እንዳልገባ ሳምንቱን ሙሉ አንሰፍስፋኝ አርብ ማታ ሲሆን ማርያም ጣቷን ዘርግታ ስለምትታረቀኝ አይደለም ። አባታቸው ከታላቅ ወንድሟ (ጅል ስለሆነ አሎደውም) ጋር አንበሳ ግቢ ለሽርሽር ወስዷቸው ስትመለስ አንበስየው እንደሳማትና እንደኔ አይነት ንፍጣም ልጅ እዛ ከገባ እንደሚባላ ስለምተርክልኝ አይደለም ። ኦፖፕ በኮዳዋ ይዛ መጥታ ተደብቀን ከንፈራችን ቀይ እስኪሆን ስለጠጣን አይደለም ። ከስልክ እንጨት ጋር የተወጠረ የሱዚ ገመድ ይዤላት . . . ጉልበት ፣ ቂጥ ፣ ወገብ . . . እያለች ስለምትዘልና ስለምትበለቀጥ አይደለም ።
-
ዱቡልቡሉ ማስቲካ አምልጧት ውጣ ወይኔ ጉድሽ ውስጥሽ አድጎ ትሞቻለሽ ብዬ ስላስለቀስኳት አይደለም ። እነሱ ት/ቤት ያሉ የእንግሊዘኛ መዝሙሮችን ስለምታለማምደኝና ስሳሳት አስሬ እየደጋገመች አሁንም አሁንም ስለምትስቅብኝም አይደለም ። እቃቃ ስንጫወት እኔ ማይክል ጃክሰን ሆኜ እሷ ሚስቴ ሆና ከዳንስ ስመጣ ቡና ስለምታጠጣኝ አይደለም ። ለመጀመሪያ ግዜ ሰማያዊ ቢራቢሮ ያለበት ነጭ ፓንቷን አስወልቄ የተቆረጠ ወሸላዋን ሳይ ስላሳቅኩባትና ደሞ ጭር ሲል ጠብቀን የብልግና ነገር ስላደረግን አይደለም ።
.
አይደለም !
.
.
.
አይደለም !
.
.
.
አይደለም!
.
ሃያትዬን የምወዳት ያላደፈችና ያላደገች እውነተኛ ታሪኬ ስለነበረች ነው ። <3

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”