Thursday, April 20, 2017

በትልቁ መጥበብ

በትልቁ መጥበብ

(ቢኒያም ሐብታሙ)

በሁሉም ረገድ ትክክል የሆነ፣ ለአንድ ህብረተሰብ ዘለቄታዊ የፖለቲካ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናና ልማትን የሚያጎናፅፍ theory(ፅንሰ ሃሳብ) የለም።
አለማችን በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ Grand የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ እሳቤዎችን አስተናግዳለች።
እነዚህ Grand theories... በወቅታቸው እንደ ሃይማኖት ተሰብከው በግለሰብ ደረጃ መስዋትነትን አስከፍለው አልፈዋል።

ደብዳቤ - ለነጭ "ቺክ"

(Bethelhem Nikodimos)
-
(ደብዳቤ - ለነጭ "ቺክ")

* * * * *

በጣም ግራ ስለገባኝ ነው በበአል ምድር ይህን ደብዳቤ የምፅፍልሽ...አምስት ጥያቄዎችን ብቻ እጠይቅሻለሁ....አፋጥነሽ መልሱን ስደጅልኝ፡፡
-
1ኛ. ለአንድ ዶሮ ሆስፒታል ሙሉ ታማሚ የሚመግብ ሾርባ የሚወጣው ሽንኩርት ሁለት ቀን ሙሉ ታበስያለሽ?

(ድፎ ዳቦ፥ የከሸፈ ህብሰት)

(Nahusenay Belay)

(ድፎ ዳቦ፥ የከሸፈ ህብሰት)

* * * * *

እዉነተኛ የድፎ ዳቦ ታሪክ
ይህ በርካታ የታሪክ ድርሳናት አገላብጬ፣ እምቅ አእምሮየን ጨማምቄ የፃፍኩት እዉነተኛ ታሪክ ስለሆነ ሁሉም ሊያነበው ይገባል።

ሃይሌ ገብረስላሴ የሸነጋውያን የምንግዜም ሞዴል


ሃይሌ ገብረስላሴ የሸነጋውያን የምንግዜም ሞዴል፣ የስኬት ልኬት ጥግ ማሳያ ፍጥረት ነው፡፡ ሃይሌ እንደ ሠገጤ አለፈልኝ ብሎ አያካብድም፣ ራሱን አይቆልልም፡፡ ስራን አይንቅም፡፡ መሠረቱን አይረሳም፡፡


-


መላው የሸነግ አባላት ለሃይሌ ገብረስላሴ የመልካም ልደት ምኞታቸውን የሚገልጹት፣ እጅግ የላቀ ክብር እየተሰማቸው ነው፡፡

-

-

(መልካም ልደት፣ ሃይሌ ኬኛ!)

ሸነጋዊ ትግላችን በቀልድ

የሸነጋችን በቀልድ የተዋዛ እና ነቄ የሚመራው ይሉኝታ ለምኔ የማህበራዊ ሂስ በትውልዳችን ውስጥ ተተኪ የሌለውና የማንም የተሸማቀቀ #ሰገጤ ሊገባው የማይችል ዘመን ተሻጋሪ ፋይዳ አለው:: እንዲህ በልባዊ ድፍረት በተሞሉ የጭሶች ቀልዶች ወይም ኒዮማርክሲስት÷ኒዮአራዳ ቧልቶችን - የሸነግን (የወትሮውን ሸንጋ ሰገጤና ወጠጤ ሳይሆን) ቦቅቧቃ÷ቆሌ የራቀውን÷ከራማው የተገፈፈውን ሽንጣም (እንዲሁም ሽንታም) ጥርብ በአራዳ ጨዋታ ሳንጃ መላ የደነዘ÷ የደነዘዘ ቂጡን እየወጉ መንጨቅ አድርጎ የማንቃት ስልት ውስጥ ስላለው የኮሜዲ ጠቀሜታ ስሎቬኒያዊው ሸነግ-ቀመስ ማርክሲስት ፈላስፋ እጩ ሸነግ Slavoj Zizek የሚከተለዉን ቅልብጭና አላፊ-አግዳሚ ሰገጤ ሰርስሮት እንዲዘልቅ አድርጎ አስፍሯል፤

"Comedy is thus the very opposite of shame: shame endeavors to maintain the veil, while comedy relies on the gesture of unveiling. More closely, the comic effect proper occurs when, after the act of unveiling, one confronts the ridicule and the nullity of the unveiled content—in contrast to encountering behind the veil the terrifying Thing too traumatic for our gaze. Which is why the ultimate comical effect occurs when, after removing the mask, we confront exactly the same face as that of the mask."
...........

እናማ ሸነጋዊ ትግላችን በቀልድ ክፍለጦር እና በሰገጤ ደምሳሽ ቁምነገረኛ ጀነራሎቹ ታጅቦና አሸንግቆ (በሸነግኛ አሸብርቆ) የሰገጤ አረም እስኪያሽልብ Aluta Continua - የሸነግ መቆማያ መቀመጫ የሚያሳጡ ሽንቆጣዎች ይነፋሉ። የሰገጤም የማይነፉ (ጅን በያለበት ይንፋው!) ስግጠጣዎች እየተነፉ ይቀጥላሉ።

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”