Friday, April 21, 2017

የአንቲ ሰገጤይዝም ንቅናቄ

(ሄኖክ ያሬድ)
-
የአንቲ ሰገጤይዝም ንቅናቄ “Prejudice” አልያም “stereotype” ነው እያሉ ስም ለሚያጠፉ ኮንፊውስዶች የተጻፈ እኛ የአራዳ ልጆች “ሰገጤ” ስንል “ገጠሬ” ብለው የሚያዳምጡ ተውሳኮች ተበራክተዋል፡፡ 
-
ስለዚህም “የሰገጤይዝምን” ሜታፎር ማስረዳት ግድ ብሎናል፡፡ ሰገጤ ስንል በፍጹም ገጠሬ እያልን አይደለም፡፡ አልያም የአዲስ አበባ ልጅ ያልሆነን ሁሉ ሰገጤ ብለን አልፈረጅንም፡፡ አማርኛን አኮላትፎ በጭንቀት መናገር ወይም ከነአካቴው አለመናገር ከሰገጤ ካምፕ አያስገባም፡፡ እንዲያውም የሌሎችን ቋንቋና ባህል ማክበርና ለመረዳት መሞከር የአራድነት የቴክስት ቡክ ዴፊኒሽን ነው፡፡ ስግጥና ከነአካቴው በድንበር አይፈረጅም፡፡ ዘር ቆጠራ ውስጥ ገብተን ለተወሰነ ዘር የስግጥና የሃፍረት ካባን አላለበስንም፡፡
-
እራሱን ከብሄር መነጽር አንጻር የሚያየውን ሁሉ ሰገጤ ነው አላልንም፡፡ እኛ የአራዳ ልጆች የህዝቦች የግለሰብና የቡድን መብት እናከብራለን፡፡ አማራ፣ትግሬ፣ኦሮሞ ወይም ሌላ መሆን እና ነኝ ማለት ሰገጤ አያስብልም፡፡ አራት ነጥብ!!!! እኛ ሰገጤ የምንለው ከእኔ አስተሳሰብ ሌላ ወደ ኻላ፣ ከእኔ ማንነት ውጪ ወደ ውጪ የሚለውን ፋሩካ ነው! ሌሎችን ለማጥላላት መንገድ የማያጣውን፣ ህዝብን በጅምላ የሚያንቋሽሸውን፣ ለልዩነት ቦታ የሌለውን፣ መጤን ለማራከስ የሚሽቀዳደመውን፣ ኢሉሚናቲ ዋን ወርልድ ኦርደር ምናምን የሚሉ ቅዠቶችን አብሮ የሚያራግበውን፣ ሃይማኖት የእምነት መንገድ እንጂ ግብ መሆኑን የማይረዳውን፣ የሌሎች ሃይማኖት እምነት ተከታዮችን መናፍቅ ካፊር ምናምን ብሎ የሚጠራውን፣ ሁሉን ነገር ከብሄር መነጽር ብቻና ብቻ የሚያየውን ፣ ቱጌዘር ዊ አር ስትሮንገር የሚለውን መርህ ያልተረዳውን፣ “ማይ የሆነ ነገር ፈርስት“ የሚለውን፣ ወ.ዘ.ተ ነው፡፡ 
-
እራሱን እንደ ኪሊማንጃሮ ሰቅሎ፣ ግብዳ የጥላቻ ድንበር ቆልሎ ሰውን የሚያራክስ ምቀኛ፣መተተኛ እንዲሁም ሟርተኛ እሱ ነው ሰገጤ ለኛ! (ፓፓፓ እቺን ግጥም ከፍቅሬ ቶሎሳ አይን ይሰውርልኝ!) ሎል #ሸነግ #ሰገጤ #Antiracialbulling

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”