[Mahi]
• • • • • •
ማስታወቂያ!!
ማስታወሻ!!
ለስራ ፈላጊዎች!!
ይሄን ያውቁ ኖራል!!
ይልሃል ባለ እድል!!!
• • • • •
"ብርዱን ኣስመልክቶ የወጣ ፍላጎትን መግለጫ"
(በፈለጉት ርእስ ማንበብ ይችላሉ)
.
ጉዳዩ:~ የፍቅር ኣጋርን መፈለግ
ፈላጊ:~እኔ
ፆታ:~ወንድ!!
እድሜ:~ከ27~34
አቋም:~ ልክ ያለው....ጡቱ ከኔ ጡት ማይበልጥ .....ኣጠገቤ ቁጭ ብሎ ወደሌላ ኣቅጣጫ እንዳላይ ማይከልለኝ....ማያሳምመኝ....
.
ማር....ቤብ...ፍቅር .....እያለ ማይጠራኝ....ኣብሶ እማ እያለ እድሜዬን ሊያስታውሰኝ ማይሞክር.....እማውን እናቱ ቤት ትቶ ሚመጣ
.
በግንኙነት ውስጥ እስካለን ሌላ ሴት ማይነካ.......ማለትም ኦቨር ታይም ማይሰራ...ማንበብ የሚወድ....ነፃና ግል...ፅ......ኣብሮኝ ሲሆን ደስተኛ የሚያደርገኝ.....ቀልድ እየለቃቀመ .....ያሳቀኝ መስሎት ማያሳቅቀኝ...
.
"ይኽውልሽማ ላስረዳሽ" እያለ ማያዝገኝ.....ስለድሮ ገርል ፍሬንዱ....ምሳሌ እያጣቀሰ ሊገስፅኝ ማይሞክር....ኣባትነትና ....ፍቅረኛነትን የለየ..... ደረቱ ላይ ፅጉር የሌለው.......ጄል ማይቀባ....ስቲም ማይገባ መታዘል ስለምወድ.....የሚያዝለኝ "መንገድ ላይ"
.
"የታመመ....ይታከማል
ያበደ....ይታሰራል
የደከመው ያርፋል
ያፈቀረ ምን ይሆናል"
እና የመሳሰሉትን.....ኣይነት ቴክስት በመተኛ ሰኣቴ እየላከ....ኣዳሬን ማያበላሽ....
.
ቅዳሜ ቅዳሜ ከኣቅም በላይ ያልሆነ ኣጋጣሚ እስካላጋጠመን ድረስ ኣብረን ኣብሮኝ ጊዜ ሚያሳልፍ...."ማደርንም ይጨምራል"
.
.
ስራ ሊኖረው ግድ ነው......ኣብረን ስንሆን ለምናወጣው የጋራ ጥቅማጥቅም ሁላ ......እንደኣልቃይዳ አባል ሃላፊነቱን በጋራ እንወስዳለን...
.
.
ስንት ልጅ ትወልጂልኛለሽ? የመጀመሪያ ልጃችን ሴት ናት ስሟ ደሞ.....ምናምን የሚል ሰላጣ ያልሆነ ወሬ ማያወራኝ....ሸሚዝ በሹራብ ደርቦ ማይለብስ.... ሹልቴክስ ቆዳ ማያደርግ....መላጣ ያልሆነ....ቻፕስቲክ ይዞ ማይዞር....ካፕል ቤት ማይወድ....መጋባትና መግባባት ያልተምታታበት....ፍሪክ ያልሆነ.....ቃና ማያይ...ሻይ በሎሚ ማይጠጣ.....ማሳጅ ቤት ማይሄድ....
.
የሸነግ ኣባል የሆነ!!!!!!!
.
ቢራ መጠጣት የሚወድ....
የግንኙነትቦታ:~ አዲስ አበባ ብቻ!!!
ክፍለሃገር ነዋሪም...ሆነ ከኣገር ውጪ ኣላስተናግድም
.
ይሄን መስፈርት የምታሟሉ ሲንግል ወንዶች.....
.
.
ኣታፍሩም እኮ እያነበባችሁ ነው....ኣይ ኣንብቡ ኣረ....እናላችሁ
.
ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 የስራ ቀናት
.
.
ፍቅር ከፈጣሪ ነውና ተግታችሁ ፅልዩ!!
.
.
(ምፅ!)
No comments:
Post a Comment