Thursday, April 20, 2017

ደብዳቤ - ለነጭ "ቺክ"

(Bethelhem Nikodimos)
-
(ደብዳቤ - ለነጭ "ቺክ")

* * * * *

በጣም ግራ ስለገባኝ ነው በበአል ምድር ይህን ደብዳቤ የምፅፍልሽ...አምስት ጥያቄዎችን ብቻ እጠይቅሻለሁ....አፋጥነሽ መልሱን ስደጅልኝ፡፡
-
1ኛ. ለአንድ ዶሮ ሆስፒታል ሙሉ ታማሚ የሚመግብ ሾርባ የሚወጣው ሽንኩርት ሁለት ቀን ሙሉ ታበስያለሽ?

2ኛ. ስትፈጊ እኩለ ሌሊት አልፎ ስራሽን ጨርሰሽ ጋደም ከማለትሽ አባወራ ባልሽ ጎንሽን "ድስቅ" አርጎ..."ተነሽ ከለሊቱ 9 ሰአት ሆኗል ፆም እንፍታ" ብሎሽ ያውቃል?

3ኛ. ፀጉር ቤት ሄደሽ በሁለት ኪሎ ዊግ ሙሉ ተቆንድደሽ ሹሩባ ተሰርተሽ አውዳመቱን የረሳውን ነገር እንዳስታወሰ ሰው ቅንድብሽ ወደላ......ይ ስቅል ብሎ ሹሩባሽ እያሳመመሽ ውለሽ ታውቂያለሽ?

4ኛ.ዘመድ ጥየቃ በማግስቱ ስትሄጅ ከስሙ በቀር ከአበሻ ሁለት እጥፍ የሚተልቅ "ያበሻ ድፎ ዳቦ " ተሸክመሽ ተጋፍተሻል?

5ኛ. እንደኔ በጉልበትሽ ተንበርክከሽ "ጌታ ሆይ በቲቪ ከሚተላለፉ የበአል ፕሮግራሞች እና ከቲቢ በሽታ ሰውረኝ" ብለሽ ፀልየሻል??

-

(አክባሪ ወዳጅሽ- ያበሻ "ቺክ")

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”