(ማሂ)
* * * * *
ኣንድ ሰፈር ነው የተወለድነው.....ቤተሰቦቻችን ጎረቤታሞች እኛ ደሞ ኣብሮኣደጎች ..... እሱዋን ለመብለጥ የማላደርገው ነገር የለም.... እቀድማታለው ከትምህርት ስንለቀቅ ቀድሜያት እቤቴ ሄጄ እራሴን የሚያክል ቂጣ ይዤ መምጫዋ መንገድ ላይ እጠብቃትና እንቁልልጭ እያልኩ ኣናዳታለው፡፡
.
.
የትምህርት ደረጃ ላይም እኔ ከፊቴ ኣርባ ተማሪዎችን ኣስቀድሜ 41ኛ ስወጣ እሱዋ ትምህርት ስለማትወድና ሰነፍ ተማሪ ስለሆነች 42ኛ ወይንም 43ኛ ነበር ምትወጣው....እበልጣት ነበር
.
ልጅ እያለን በክረምት ዝናብ መሃል ብልጭ የሚለውን መብረቅ ከእህቶቼ ጋ እወጣና ተቃቅፈን እግዚያብሄርዬ ብልጭ ኣድርጎ ፎቶ ያነሳናል እያልን ለቤቱዋ ብቸኛ ልጅስለሆነች እህት የሌለው ሰው ፎቶ ኣይነሳም እያልኩኝ የጎሪጥ እያየው ኣስለቅሳት ነበር
.
ሽንት ቤት ይዛው ልትገባ ያዘጋጀችው ውሃ ውስጥ ሚጥሚጣ ጨምሬ ኣስቃጥያታለው
.
5ተኛ ክፍል ኣይኖ ዘኪለር ስንጫወት ቀን ጠብቃ የክፍላችንን ብዙ ንፍጥ የሚወጣውን ልጅ ኣስማኛለች
.
አዲስ የተገዛልኝን ረጅም ቀሚስ እናሳጥረውና ኣጭር ቀሚስ ይሁንልሽ ብላ በምላጭ ቅድድ ኣርጋብኛለች
.
ሳማ እየቆረጡ እያመጡ የሚያስገርፉንን ኣሮጊት መታመማቸው ሰምታ መታ በትልቅ ሰሃን ውሃ ይዘን ሄደን ይቺን ምግብ ይብሉ ብላ የሱዋ እናት ነው የላከችው ብላ ተይዘን በሳማ ቂጣችን እስኪቀላ ተገርፈናል....
.
ኤለመንተሪ ሳንጨርስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን መቃብር ቦታ የአበበ በቂላ ሃውልት ላሳይሽ ብላ የሰፈራችን እማማ ትልቋ ሲሞቱ...... የእናቶቻችንን ቀሚስ ለብሰን ለቅሶተኛው የሚሄድበት ሎንቺና ውስጥ ጥልቅ.......እዛ እንደደረሰን በሷ ጋይድነት መቃብር ለመቃብር ስንዞር ውለን መኪናው ትዘንጥበታለች አምልጦን ...... ያየነው ስቃይ
.
ትምህርት ቤት እናትና አባት የሌላችሁ መረዳት ምትፈልጉ ሲባል እጅ ለማውጣት ማንም አልቀደመንም .... የተቀበልነውን ቱታ እንደውም እስካሁን ታናሽ እህ
.
ሰንበት ትምህርት ቤት የጥምቀት መዝሙር ልናጠና ሄደን ከፊት የተሰለፉትን ልጆች ነጠላና ነጠላ አስረን እንዲወድቁ በማድረጋችን.... "ማጋይቨር " ከሚል ቅጥል ስም ጋ እንዳንሰለፍ ተባረናል......፡፡
ከቤተክርስቲያን የተባረርን የመጀመሪያዎቹ ልጆች ሳንሆን አንቀርም ነበር፡፡
ወረቀት ጠቅለን ሴሽ ሴሽ .. ተጫውተናል......፡፡
...
ብንዋደድም አንዳችን ከአንዳችን ላለመበላለጥ የምናደርገው ጥረት ያስቅ ነበር...አንድ ቀን ብዙ ጠላ በመጠጣት ማን እንደሚበልጥ ተከራከርን..... ውድድር ተጀመረ
አልቻለችኝም በለጥኳት!! ተናደደችና መታችኝ ተደባደብን ተያይዘን ወደቅን ጩኽታችንን
ሰምተው የመጡት ቤተሰቦቻችን ሲያነሱን እሷ የፊት ጥርሷ አጥታ ነበር....አብረን
እንዳንጫወት ተከለከልን ....ብዙም ሳይቆዪ ሰፈር ቀየሩ
.
ስለምበልጣት ሰፈር ቀየረች ብዬ ደነፋው
.
.
ዛሬ ከስራ ወጥቼ በመንገዴ ያየሁዋትን ቀሚስ ልጠይቅ ከጔደኛዬ ጋር ወደ ውስጥ ገባንና እንድለካው ጠየኩት ለካውትና ወደውጪ ወጣው... ቀሚሱ ትንሽ ሰፍቶኛል
መስታወቱ ጋ ስቆም ሻጩ ወጣት በጣም ነው ሚያምርብሽ ግን ጡት ስለሌለሽ ደብል ስፖንጅ ማድረግ አለብሽ.... አየሽ ይሄ ቀሚስ ተለቅ ያለ ጡት ያላት ሴት ብታደርገው
ልክ እንደሷ አለና ወደበር ሲጠቁም "ምናባቱ ጡት ጡት ይላል ጠብቶ አላደገም እንዴ ? እያልኩ ቀና አልኩና አይቼ ጎንበስ.....ከዛም በፍጥነት ቀና ብዬ እይታዬን ደገምኩት.....፡፡
እ
ራ
ሷ
ናት....ተያየንና ጩኽታችንን ለቀቅነው፡፡ ሄጄ አቀፍኴት.....ረጅም ሰላምታ ተለዋወጥን
ቀሚስ ፈልጋ እንደመጣች ነገረችኝ.... ሻጩ ምልልሳችንን እየሰማ ነበርና አፈርጋጣሚው ስሆንልሽ የለበሰችውን ለኪው..... ቅልቅልቅል ሲል ሲያስጠላ.... እስቲ ልሞክረው
ስትል አውልቄ.... ሰጠዋትና መቀየሪያው ክፍል ገብታ ለብሳው ወጣች...... ስታምርየሚለው ቃል አይገልፅውም.....ዞር ዞር ብላ አሳየችን.....እንዴት እንደሚያምርብሽ አለና ወደኔ ዞሮ አየሽ እሷ ጡት !!!! ስለምትበልጥሽ !!!!! ቀሚሱ እንዴት እንዳማረባት .....ሲል ቀና ብለን ተያየን ላለመበለጥ ያጣቻት ጥርሷ ላይ ሰው ሰራሽ ጥርስ ተተክሎላታል ፈገግ አለች...... እንደልጅነታችን አልተቀናናንም.... ይልቅ ወደኃላ መለሰንና.... ተቃቅፈን ተሳሳምን....ቀሚሱን ገዛችና ወጣን..........ወይ እዝጌር ካልቸገረው ነገር በጡት ያስበልጠኝ ??? ይልቅ ቀሚስሽ ትንሽ ቢያጥር ያምራል ላሳጥርልሽ ስላት መንገደኛው ዞር ብሎ እስኪገረምመን ድረስ ጮክ ብላ ሳቀች.......፡፡
ናፍቃኝ ነበር!!
.
ስንለያይ!!!!
.
መንግስትና ጡት መውደቃቸው ኣይቀርም.. ወይንስ looking for ጡት ለማሳደግ
የሚረዱ ዘዴዎች የሚል ፖስት ልለጥፍ .. ምን ልልም እንደሆነ ሳላውቅ ስልኬን......... ኣወጣው።
.
.
.
ፅድት ያለ ቅዳሜ ለመላው ሸነጋውያን!

No comments:
Post a Comment