Saturday, April 22, 2017

የሸነግ ማእከላዊ ኮሚቴ የሠጠው መግለጫ

"በክቡር መተኪያ"

የታፈርክ የተከበርከው የሸነግ አባልና ደጋፊ ሆይ ድርጅትህ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሮልካል...

(የሸነግ ማእከላዊ ኮሚቴ የሠጠው መግለጫ)

የግፍ አገዛዝን እምቢኝ ብለው ጥቂቶች ጫካን ዱር ቤቴ ብለው ከገቡ በሁዋላ ዛሬ ሺህ ምንተሺሆችን ማሥከተል የቻለው ሸነግ ኮተቤ አካባቢ ይገኝ ከነበረ ባለ 15 ችግኝና ባለ 11 የቀረሮ ዛፍ የማዘዣ ጣብያ ወጥቶ ዛሬ ለሚገኝበት ባለ ሁለት ሺህ ላይክ ፔጅ ደርሡዋል...


እንደነ ዘውዳለም ታደሠ አይነት የእናት ጡት ነካሾችን በተደጋጋሚ ሂሥና ግለ ሂሥ አውርዱ ሥንል እነርሡ ግን በተደጋጋሚ የገንዘብ ያዥነት ሥልጣን ካልተሠጠኝ በማለታቸውና ጥያቄያችውም ተቀባይነት በማጣቱ ዛሬ ከሚገኙበት የጸረ ሸነግ ህቡእ ድርጅት ውሥጥ ሆነው ድርጅቱ ባጀት የለውም እያሉ አላማቸው አልሣካ ሢል የሥም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱብን ይገኛሉ።

ይሁንና ይህ ባለ አንድ ግዙፍ ላይክ ፔጅ ድርጅት እንኩዋን ፎቶ በሌለው በአንዲት አይጥ ፕሮፋይልነት በሚንቀሣቀሥ በነ ዘውዳለም አይነት ሠዎች ይቅርና በአባታቸው በጉምቱ ተቃዋሚ (መረራ ጉዲና)በአያታቸው የአንድ ትልቅ የሀገሪቱን ኤፍ ኤም ሬድዬ ሥም(ፋና ኤፍ ኤም) በያዙት በአቶ ገመቹ መራራ ፋና ሊደናቀፍ አመመቻሉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው።


ሸነግ የህዝብ እና ከህዝብ የተገኘ ጸረ ሠገጤ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ይህንን በማእከልነት የእዝ የሥልጠናና የፕሮፓጋንዳ ማእከል ፔጃችን ጃም እንዳይደረግ ከየትኛውም አቅጣጫ እሚሠነዘርበትን ሞገድ ለመቁዋቁዋም ሥትሉ ረዘም ያለ አንቴና በዋኪቶኪያችሁ እንዲሁም በሥልካችሁ ላይ ገጥማችሁ በቀን ለ 10 ደቂቃ ያክል እሚሠራጨውን ሥርጭት እንድትሠሙ ብሎም ከዚህ ከማእከላዊ እዝ ውጭ የሚሠራጭ ማንኛውም ፕሮፓጋንዳ ይሁን ትእዛዝ ተቀባይነት እንደሌለው እንድታውቁ ሥንል በጥብቅ እናሣውቃለን


ፊርማ የማይነበብ...


ሸነግ የህዝብ ነው.


ሸነግ ያሸንፋል..


ሠማያዊ ሽብር ጸረ ሸነጋውያን ላይ.


ሸነግ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ


No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”