Saturday, April 22, 2017

ያዲስ አ'ባ ልጆች!

ያዲስ አ'ባ ልጆች!

(ዘውድአለም ታደሰ)
-
-
-
ዘር እየቆጠሩ
ብሄር እየጠሩ
ሲያቅራሩ ቢውሉ ፣ አይበርደን አይሞቀን
ላ....ሽ ነው የምንለው እንዲያው ተሳስቀን።


አይጥመንም እኛ፣
ጥላቻናን ክፋት ፣ ተራ የቤት ጣጣ
ተ....ቄ ነው ምንለው፣
ብሄር ብሄር የሚል ወጨጌ ሲመጣ!
ህዝቤ ሲነታረክ
የጎሳ፣ የብሄር፣ ጭቅጭቅ ሲፋፋም
'ባላየ ተሸብለል ሙዳቸው አይነፋም'
ተባብለን ምንርቅ ከችኮ ባላገር
ድንበር ማያግደው ፍቅር ነው የኛ ሃገር!
ከሰው እስከሰው ነው ሩቅ ነው የኛ ድንበር
ከተመቸን ጋራ ብሄር ሳናሰላ ከፍ ብለን ምንበር።
ሰንዝረው ማይይዙን የጥላቻ እጆች
እንደዚህ ነን በቃ .... ያዲስ አባ ልጆች!
ኳስ እንዳንጫወት ሳቢ ሲጠርብን
አምና ሜዳችንን ሼኪው ያጠሩብን
በእትብታችን ላይ ህንፃ ሲቀልሱ
ኩርማን ጎጇችንን በዶዘር ሲያፈርሱ
«ትርፉ ትዝብት ነው» ብለን ሙድ የያዝን
ቀልድ የምንፈበርክ ቢከፋን ፣ ብናዝን!
ካንዱ ሲያባርሩን ፣ የሚከፈቱልን እልፍ አእላፍ ደጆች
ቢገፉን የማንወድቅ፣ እንደዚህ ነን በቃ .... ያዲስ አባ ልጆች!

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”