Saturday, April 22, 2017

የሸገር ታሪካዊ አመጣጥ

(Addisu Engidawork)

* * * * *

የሸገር ታሪካዊ አመጣጥ በመረቅኛ
1) መጀመሪያ ተጠመቅን.....
"ከዕለታት አንድ ቀን 'ጣይቱ' የተባሉ እቴጌ እዛች ፍልውሃ የምትባለው የምትጤስ ቦታ፣ እዛች እርጥብ ፊንፊኔ ገላቸውን ተታጣጥበው ጨርሰው፣ ከተቀመጡበት በርጩማ ብድግ ሲሉ፣ እንደ ደንግ የምታበራ የህልም እንቁላላቸው የምትሞቅ ግልገል ኩሬ ውስጥ ወደቀች...."


2)መከባበርን ለዓለም አበሰርን....
" ከዛም ወደ ተሰራላቸው ማረፊያ ጎጆ አቀበቱን ሲያዘግሙ፣ ስሟ የተጠራ ከተማ የመቆርቆር ምኞታቸው ከአንደበታቸውና ከረጠበ ጉንጉናቸው በሚያልፉበት ጎዳና ላይ ተንጠባጠበ።ባለቤታቸው ንጉሠ ነገሥት ሚኒሊክን ጨምሮ ሕዝቦች ያን ከፍልውሐ ጉም እስከ ባዕታ ወይራዎች ድረስ የተዘራውን የእመቤታቸውን ምኞት አተኩረው እንደ ጥሬ ለቀሙ (ምንም እንኳን በንግርት ባላቸው እንጦጦ ላይ የታፈረ መንግስት እንዲያቆሙ ንግርት አለ ቢባልም)።...."

3)የምናረገው እንደምናውቅ ለሰገጤው አረጋገጥን....
"ቅጠል በልቶ ከተነበየ ባህታዊና አውቃለሁ ባይ የአምደ ፅዮን ዘመን ደብተራ ይልቅ ጎርጎራ ከተማ በጣና ዳር በመረጋጋት የሰለጠነ የንግስት ጣይቱ ድምቡሼ ገላ ትንቢት አሸነፈ።....."

4)በመጨረሻም እነሆ ገፀ-በረከት....
"ብዙም ሳይቆይ ሚኒሊክ እንጦጦ ማርያም ግቢ ጉባኤ ጠርተው መኳንንቶቻቸውን እንዲህ አሉ:-
<<አዲስ አባን እንካችሁ። ተጠራርታችሁ ሙሏት>>"
.
.
.
ማጣቀሻ ፣ አዳም ረታ፤ መረቅ
.
.
.
.
ሸነግ አዳኜ ነው!!
ሸነግ መታመኛዬ ነው!!
ሸነግ ህይወቴ ነው!!
ሸነግ ይለምልም!!
ሸነግ ያብባል!!
የሽነግ ቢጫ ሽብር ይፋፋም!!(አደይ መሆናችንን ልብ ይሏል)

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”