Saturday, April 22, 2017

ሸነግን ከክሽፈተ እንታደገው

(Henok Yared)

ሸነግን ከክሽፈተ እንታደገው

ምንም እንኳን አስቀድመን የጀመርነውን የአራዳ ልጆች ነጻ አውጪ ግንባር ንቅናቄ እዮብ በሚባል የኡሩጉዱሩ ላቦሮ በጓሮ በር ብንነጠቀም .... ለግል ስልጣን በመሻኮት የአራዳ ልጆችን ተጋድሎ አናኮላሽም በሚል ማርስ በሚደርስ ሆደ ሰፊነት የሸነግ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ ወስነናል!

ሆኖም ሁሉም የአራዳ ልጆችን ያሳተፈ ትግል ማካሄድ እስካልቻልን ድረስ ለኛም መክሸፍ እንደ ሸገን የሚል መጻሃፍ ነገ በአንዱ ሽማግሌ ፕሮፌሰር ተብዬ ስላለመጻፉ ምንም ዋስትና የለንም! ስለዚህም የሸነግ እንቅስቃሴ በመላው ኢትዮጵያ (በናዝሬት፣ በደብረዘይት፣ በድሬ፣ በሃረር፣ በአሶሳ፣ በጋምቤላ፣ በመቀሌ፣ በባህርዳር …… ጎንደር፣ወለጋና አምቦ ሲቀሩ በመላው ኢትዮጵያ) ማስፋፋት ይቻል ዘንድ በትግሉ ላይ የስያሜና የራእይ ማስተካከያ ተደርጎ ሁሉንም የአራዳ ልጆች ያሳተፈ ንቅናቄ እንድንመሰርት በትህትና እንጠይቃለን! 

(ኖት፡- ጎንደር፣አምቦ እና ወለጋ ዲፕሎረብል እሳት ላይ ቢጣዱም የማይበስሉ ስለሆኑ እነሱ ላይ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም)

የአራዳ ልጆችን ትግል ወደ ሸገር ብቻ ማውረድ ልክ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የአራዳ ልጆች ትግል የብጣሽ መሬት ግብግብ ሳይሆን የማንነት ቅበላ የማግኘትና ሃሳባዊ ልእልናን መፍጠር በመሆኑ ትግላችንን በድንበር ማጠር ማቆም አለብን! የፋራና የሰገጤ የ2016 ዓመተ ዓለም አስተሳሰብ በተደራጀ መልኩ በዚህ ዘመን መምታት ካልቻልን ለሚቀጥለው ትውልድ የአራዳ ልጆች የልቀት ሂደት ላይ ሳንካ ተክለን እያለፍን እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል!

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”