“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”
Friday, April 21, 2017
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
በአነግ (የአራዳ ልጆች ነጻ አውጪ ግንባር) የታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
-
ዲር ጀለስካ ተንቀናል፣ተዋርደናል ብታምንም ባታምንም በቁማችን ሞተናል!
-
እኛ ሰው ባደረግናት ከተማ ጎሩጊሮጋራጌሪ ከሚባል ፓስፊክ ኦሺን በግራ ታጥፎ ካለ ሰፈር የመጣ ሰገጤ ጢባ ጢቢ ……. አንዴ እደግመዋለሁ ጢባ ጢቢ ….. ሲጫወትባት አይተን እንዳላየ እስከመቼ!
Read more »
ሂሥ እና ግለ ሂሥ
ሂሥ እና ግለ ሂሥ በሸነግ ምክር ቤት...
(ክቡር መተኪያ ሀይለሚካኤል)
ባሣለፍነው ሣምንት የሸነግ ጠቅላላ ጉባኤ በአባላቱ በፖሊት ቢሮ ቊዋሚና (ቃሚና) በተጠባባቂ አባላቱ እንዲሁም በሥራ አሥፈጻሚው አባላት ላይ ሂሥና ግለ ሂሥ ሢያካሂድ በመቆየቱ እንቅሥቃሤው በሠገጤዎች የተገታ የመሠላቸው አንዳንድ በውጭ ሀገር በርገራቸውን የሚበሉና ድርጅታችንን ለማተራመሥ የሚፈልጉ ጸረ ሸነጎች ፕሮፓጋንዳ እየነዙ እንደሆን ደርሠንበታል..
Read more »
ሸነግት
(እሸቱ ሃይሌ ሸነግት መንፈስ ነው ይለናል)
* * * * *
እኛ ሸነግ የሆንን የሸነግ አባል ሁሌም የምንዘመረው አንድነት ነው፡፡ ሸነግ ስትሆን ኢትዮጵያዊነት ውስጥህ ነው ሸነግ ስትሆን ፍቅር ይገዛሀል በአይን ለምታውቀው የእካባቢህ ልጅ ታክሲ ውስጥ ትከፍላለህ ወይይከፈልልሀል፡፡ ሸነጎች እንዲህ ነን፡፡ ሸነግ ማለት አንድነት አንድነትም ሸነግነት፡፡ ይሔ ዘረኝነት የእገሌ ብሔር ጭውቴ አትመቸንም፡፡ ትግራውያንን ሁሉ ወያኔ ማለት ይደብረናል፡፡ አማራን ሁሉ ነፍጠኛ ይደብረናል፡፡ የኦሮሚያን በደል ያነሳውን ሁሉ ኦነግ ማለት ይደብረናል፡፡
-
ብዙ ነገሮች ቢደብሩንም ኢትዮጵያዊነት ግን ከነ ንፍጡ እንወደዋለን፡፡ ለምን ብትሉ ሸነጎች ነና፡፡
ሸነግ ደርቢ
ሸነግ ደርቢ
1. ሸነግ ደርቢ ዛሬ ነው
:)
2. የሸነግ አባል ለሆናችሁ በሙሉ "አግ7" የሚለውን የጥምረት ስም ስታዩ ፓስዎርድ በቀላሉ እንዳይሰረቅ የተዘየደ የቃላትና የቁጥር ጥምረት መስሏችሁ እንዳትሸወዱ ይሁን
:P
Read more »
የሸነግ አሥርቱ ትዕዛዛት
ከወንበዴው እዮብ ምህረተአብ
( የሸነግ አሥርቱ ትዕዛዛት)
* * * * *
(1)
ሸነጋዊነት ማለት ስልጡን ማንነት፣ የከተሜያዊ ስብዕና ባለቤት መሆን ማለት ነው፡፡ ከ Regional Boundary ጋራ ንኪኪ የለውም፡፡ እንኳንስ አዲስ አበባ ተወልደህ፣ ኒውዮርክም እየኖርክ ሰገጤነት ላይፋታህ ይችላል፡፡
ሸነጋዊነትን በወንዜ ልጅ መለኪያ መመዘን በራሱ ሰገጤነት ነው፡፡
Read more »
የአንቲ ሰገጤይዝም ንቅናቄ
(ሄኖክ ያሬድ)
-
የአንቲ ሰገጤይዝም ንቅናቄ “Prejudice” አልያም “stereotype” ነው እያሉ ስም ለሚያጠፉ ኮንፊውስዶች የተጻፈ እኛ የአራዳ ልጆች “ሰገጤ” ስንል “ገጠሬ” ብለው የሚያዳምጡ ተውሳኮች ተበራክተዋል፡፡
-
ስለዚህም “የሰገጤይዝምን” ሜታፎር ማስረዳት ግድ ብሎናል፡፡ ሰገጤ ስንል በፍጹም ገጠሬ እያልን አይደለም፡፡ አልያም የአዲስ አበባ ልጅ ያልሆነን ሁሉ ሰገጤ ብለን አልፈረጅንም፡፡ አማርኛን አኮላትፎ በጭንቀት መናገር ወይም ከነአካቴው አለመናገር ከሰገጤ ካምፕ አያስገባም፡፡ እንዲያውም የሌሎችን ቋንቋና ባህል ማክበርና ለመረዳት መሞከር የአራድነት የቴክስት ቡክ ዴፊኒሽን ነው፡፡ ስግጥና ከነአካቴው በድንበር አይፈረጅም፡፡ ዘር ቆጠራ ውስጥ ገብተን ለተወሰነ ዘር የስግጥና የሃፍረት ካባን አላለበስንም፡፡
Read more »
የሸነግ አቋም
ይህ የሸነጋዊነትና የሸነግ አቋም ነው::
ከአራቱ የሃገር ምሰሶዎች አንዱ.......
(ክቡር መተኪያ ሃይለሚካኤል)
ሁሉም ሙያ በራሱ ክብር የሚሰጠውና የማይናቅ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ግን አራት የአንድነት አውድ ሆነው ሃገርን እንደ ድንኳን ወጥረው ያቆሙ የህልውና መሰረት የሆኑ ሙያዎች አሉ::
Read more »
የሸነግ የአቋም መግለጫ
(ባለ 10 ነጥብ የሸነግ የአቋም መግለጫ)
* * * * *
(1)
ሰገጤ ሰው የሴትን ቂንጥር ይተለትላል፣ ይቆርጣል፡፡ የሴትን ብልት ሶሉ እንደተገነጠለ ጫማ ይሰፋል፡፡
(2)
ሰገጤ ሴትን ይደፍራል፣ ይጠልፋል፡፡ ይደበድባል፡፡ ያንጓጥጣል፡፡
Read more »
ታላቅ ዜና
ታላቅ ዜና ለስፖርት አፍቃሪ እንዲሁም አዲስ አጀንዳ ናፋቂ ሸነጋውያን…
-
ሸነግ የነቄዎች ግንባር ነው።
ነቄዎች ደግሞ ከሰገጤ እሰጥ አገባ ቶፒኮች የፀዱ ፍተላዎችና ሙድ መያዞች በዘለለ… የሽቀላ ንፋስ አመጣሽ አጀንዳዎችን፣ ማለትም… እናት አገሬ፣ ብሄሬ፣ ሐይማኖቴ፣ እቴቴ… ወሬዎች የፀዳ ስብስብ ነው።
የሰሞኑን የፌስ ቡክ ፀዴ ሙድ መያዣ አጀንዳ እጥረት ከግምት ውስጥ በመክተት… የሸነግ ግብር ሀሌታው ሀ ግብር ከፋይ ከፍተኛ ባለሃብት አባሎች የሚሳተፉበት… ፀዴ የእግር ኳስ ቡድን ለማቋቋም እንቅስቃሴ ላይ ነን።
Read more »
የሸ.ነ.ግ Business Trend Analysis Report
(ወቅታዊ የሸ.ነ.ግ Business Trend Analysis Report)
* * * * *
ገተታ በሌለው፣ በወደ ገደለው አነጋገር፡
ፊንፊኔ የኦሮሚያ መቀመጫ ከሆነች አይቀር፣ ድሪባ ኩማ የሸገር ከንቲባ ከሆነ አይቀር፣ ፊንፊኔ ዙሪያ ወደፊት መሬት ገዝተን ቤት ሰርተን ልጅ የምናሳድግበት ብቸኛው የማርያም መንገዳችን ከሆነ አይቀር (ምፅ!) (ምፅ!)
-
ብሄር አልባውና እጅግ ጸዴው፣ እግዜር እጁን ታጥቦ የሰራው የአዲስ አበባ ልጅ ከኦሮሞ Economic Revolution የድርሻውን ሊያገኝ ይገባል፡፡
Read more »
የመጀመሪያይቱ
ይህ የቀልድ ሳይሆን እውነተኛ ግጥም ነው፡፡ ግጥሙን አሳትሞት፣ የዱሮው የ2004 ዓ.ም ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ነው ያነበብነው ፡፡
-
ሰገጤ ምን አይነት ዥልጥ ፍጥረት መሆኑን እርስዎ አንብበው ይፍረዱ፡፡ ይዝናኑ፡፡
-
“የመጀመሪያይቱ”
መጣች ዲሞክራሲ እንደ ሃረግ ተመዛ
ሳይበሉ ሚያጠግብ እንጀራዋን ይዛ
እንኳን ደህና መጣሽ ካለሽበት ሃገር
እኒያ ጠላቶችሽ ትቅር ብለው ነበር
Read more »
ሸነግ ትለምልም!
ከሸነግ ጋር ወደፊት!! ሸነግ ትለምልም!
(ዛፍ ናት)
😀
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)
Sheneg (ሸነግ!)
“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”