Thursday, April 20, 2017

ሸነጋዊ ትግላችን በቀልድ

የሸነጋችን በቀልድ የተዋዛ እና ነቄ የሚመራው ይሉኝታ ለምኔ የማህበራዊ ሂስ በትውልዳችን ውስጥ ተተኪ የሌለውና የማንም የተሸማቀቀ #ሰገጤ ሊገባው የማይችል ዘመን ተሻጋሪ ፋይዳ አለው:: እንዲህ በልባዊ ድፍረት በተሞሉ የጭሶች ቀልዶች ወይም ኒዮማርክሲስት÷ኒዮአራዳ ቧልቶችን - የሸነግን (የወትሮውን ሸንጋ ሰገጤና ወጠጤ ሳይሆን) ቦቅቧቃ÷ቆሌ የራቀውን÷ከራማው የተገፈፈውን ሽንጣም (እንዲሁም ሽንታም) ጥርብ በአራዳ ጨዋታ ሳንጃ መላ የደነዘ÷ የደነዘዘ ቂጡን እየወጉ መንጨቅ አድርጎ የማንቃት ስልት ውስጥ ስላለው የኮሜዲ ጠቀሜታ ስሎቬኒያዊው ሸነግ-ቀመስ ማርክሲስት ፈላስፋ እጩ ሸነግ Slavoj Zizek የሚከተለዉን ቅልብጭና አላፊ-አግዳሚ ሰገጤ ሰርስሮት እንዲዘልቅ አድርጎ አስፍሯል፤

"Comedy is thus the very opposite of shame: shame endeavors to maintain the veil, while comedy relies on the gesture of unveiling. More closely, the comic effect proper occurs when, after the act of unveiling, one confronts the ridicule and the nullity of the unveiled content—in contrast to encountering behind the veil the terrifying Thing too traumatic for our gaze. Which is why the ultimate comical effect occurs when, after removing the mask, we confront exactly the same face as that of the mask."
...........

እናማ ሸነጋዊ ትግላችን በቀልድ ክፍለጦር እና በሰገጤ ደምሳሽ ቁምነገረኛ ጀነራሎቹ ታጅቦና አሸንግቆ (በሸነግኛ አሸብርቆ) የሰገጤ አረም እስኪያሽልብ Aluta Continua - የሸነግ መቆማያ መቀመጫ የሚያሳጡ ሽንቆጣዎች ይነፋሉ። የሰገጤም የማይነፉ (ጅን በያለበት ይንፋው!) ስግጠጣዎች እየተነፉ ይቀጥላሉ።

No comments:

Post a Comment

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”