Saturday, October 14, 2017

ልኡል ዘ ወልደ ከ "ቼ በለው!" ( ቼ በለው - Che Belew) መጽሃፍ ላይ Gender - of the Urban context የተሠኘውን፣ በጣም ብዙ ሰዎች ኢሞሽናል ሆነው የወደዱት የኂሩት ያለበትን ቀደዳዊ አጭር ልብ ወለድ እንዲህ አድርጎ ሪቪው አድርጎታል፡፡

-

ልኡል www.leoulzewelde.wordpress.com የተሰኘ ብሎግ አለው፡፡

-

ቼ በለው ገበያው ላይ በደንብ ገብቷል፣ ተደጋሞም ታትሟል፡፡ በወፍ ዘለል ሳምፕሊንግ ከሄድን መጽሃፉን ገዝተው ካነበቡት ውስጥ ወደ 95 ከመቶ የሚሆኑት ወድደውታል፡፡ የመጬ ተመችቷቸዋል፡፡ቼ በለውን ለማንበብ የከተማውን አዟሪዎችን ብትጠይቅ ታገኘዋለህ፡፡ ካልሆነም በከተማው ያሉ ዋና ዋና መጽሃፍት ቤቶች ውስጥ ታገኘዋለህ፡፡

-

ቼ በለውንማ ገዝተህ ማንበብ አለብህ፣ ከምር! And please like the book's Page, ቼ በለው - Che Belew,

Thanks ahead ...

-

Je vous remercie ብለናል፣ ጓድ Leoul Zewelde

-

-

-

-

-

(ፆታዊ ክህደት - የኂሩት ሴታዊ ፅናት)

* * * * *

[ ዳሰሳ - በልዑል ዘወልደ ]

መፅሐፍ - ቼ በለው - ከገፅ 16-21 ማንበብ
Gender - of the Urban context
ደራሲ - እዮብ ምህረትአብ ዮሐንስ
ዋጋ - 60 ብር

-

" Gender - of the Urban context " - ይሄ ቀደዳ ቼበለው መፅሐፍ ላይ ሁለተኛውን ምዕራፍ ይዞ ይገኛል ። መፅሐፉ በባለፈው አመት በእዮብ ምህረተአብ የተፃፈና የእንደወረደ ወሬ ይዘት ያለው የአጫጭር ቀደዳዎች መድብል ነው ።

በዚህ ከላይ በርዕሳችን በጠቀስነው ምዕራፍ ስር ከዘጠኝ መቶ በላይ አማርኛ ቃላት ፤ 78 በእንግሊዘኛ የተተየቡ ቃላት (ርዕሱን ሳያካትት) ፤ ሀያ አንድ በቅርፅ የሚለያዩ አንቀፆች ተካተዋል ።

አብዛኞቹ የተገለፁት ቦታዎች 'እዚህ' የሚል ትርጓሜ ሲኖራቸው ሁለተኛ ዲግሪዋን ለመስራት ከሀገር ውጪ እንደወጣች በአንድ ቃል ብቻ ታትቷል ። ሙሉ አተራረኩም መሳጭ የገላጭ 'Descriptive narration' ዘይቤን የተከተለ ነው ።

የሚከተሉት ዘጠኝ ገፀባህሪያት እንደአመጣጣቸው በቅደም ተከተላቸው በቀደዳው ተሰድረዋል ። አቶ ደሙ - ኂሩት (ዋና) - የመጀመሪያ ፍቅረኛዋ - የልብ ሴት ጓደኛዋ - ፌሚኒስት ጓደኞቿ - ሁለተኛ ፍቅረኛዋ - ሶስተኛው ፈረንጅ ፍቅረኛ - አንዱ ተብሎ ማንነቱ የተሰወረ (የወለደችለትና አራተኛዋ ወንድ ሊሆን የሚችል ) - እንዲሁም እራሱ ደራሲው ናቸው ።

-

(. . . መግቢያ)

በመግቢያው ላይ የዋና ገፀባህሪዋን ኂሩት ቅድመ ታሪክ ጨምሮ የተለያዩ ማንነቶች ፣ ፀባዮችና የፀባይ ለውጦች በየተራ ሲተዋወቁንና ሲገለጡ እናያለን ። ምርቃት - ምክር - ጭዋነት - ጉብዝና - ታታሪነት - ሰው ሰሚነት - ንፁህ አፍቃሪነት - መሰዋዕትነት - ክህደት/መከዳት - እያወቁ አላዋቂ መሆን - ተንኮል - ንዴት - ፀፀት የመሳሰሉት ወደተፈለገው ዋና ታሪክ ማለትም በሶስቱ ምሰሶዎችን ውስጥ ባሉ ተሞክሮና ግብረመልስ እያዋዛ ያንደረድረናል ።
በታሪኩ መጀመሪያ አቶ ደሙ የቤቷ ምርቃት ላይ ተገኝተው ዲስኩር ሲያቀርቡ ሳለ እንዲህ የሚል ያልተቋጨ ዓ.ነገር እናገኛለን ።

" ምንም ቢሆን ሴት ልጅ ያለባል . . ."

( አምስተኛ መስመር ላይ )

እንዚህ ነጠብጣቦች ከርዕሱ አወጣጥ ጋር የተገናኘ አውዳዊ ፍቺ ሊኖራቸው ይችላል ። ወይንም አቶ ደሙ ይህን ከማለታቸው በፊት የተጠቀሙትን ዓ.ነገር ያየን እንደሆነ የተወከለው ማህበረሰብ (ከተሜው) ሴት ልጅ ባል እስካላገባች ድረስ ሙሉ ክብር አይኖራትም ብሎ እንደሚያምን ሊያስተላልፍ ፈልጓል ። ይህን እሳቤ መተንተን የዚህ ፅሁፍ አላማ ስላልሆነ ትቼዋለሁ ።

በስድስት ገፆች ውስጥ ከቅድመ ታሪክና መውጫ ውጪ በሶስት አንጓ ወይንም 'የህይወት ኩርባ' ታሪክ የተከፋፈሉ ዋና ዋና ፍጭቶችን እናገኛለን ።

(. . . ሀ)

ኂሩት ከምንም አንስታ ሰው ባደረገችው ወንድ የደረሰባት ክህደትና በእርሷ ላይ ባሳደረው ጠባሳ ወንድ እርም የምትልበት ክፍል ነው - ከዛ አልፋም ትጠላለች።

በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውድ ሁሉ የወንድ የበላይነት መወገድ ይኖርበታል በማለት አክራሪ ራዲካል ፌሚኒስት ሆና እናያታለን - መሰሎቿን ትወዳጃለች ። ሲቆይና ሌሎች አጋሮቿ ቀስበቀስ ዞር ሲሉና ትዳር ሲይዙ ደግሞ መልሳ ትበረግጋለች - ለምን ? ።
ይህ የሆነው የተነሳችው በጊዜያዊ ጥላቻ እንደመሆኑ የቆመችበት የሴታዊነት ርዕዮት ሞቲቭ አለመደንደን ምክንያት ነው ባይ ነኝ ። ኂሩት መሰረታዊ የወንድ ጥላቻ የለባትም ።
መሰረታዊ የወንድ ጥላቻ መነሾዎች ውስጥ አንዱ( you need to explain this more) ቤተሰብ ውስጥ ያለ የአባት ሁከተኛነት እንደሆነ Dale O'leary " The Gender Agenda: Redefining equality በሚለው መፅሐፉ ይገልፃል ። ይህን ይዘን ወደመጀመሪያው ገፅ የሄድን እንደሆነ ኂሩት ያልተዝረከረከ መልካም ቤተሰብ ውስጥ መወለዷን አበክሮ ይናገራል። ሌላው ለዚህ አሳማኝ ኩነት በተለያዩ ወንዶች የደረሰባት ክህደት በወንድ ላይ ያላት እምነትን ፍቆ ከናካቴው ሲያጠፋው አይታይም ።

(. . . ለ)

በዚህኛው የህይወቷ ኩርባ የመሸነፍ ስሜቷ ሙሉ ለሙሉ ተስፋዋን ወደ ሀይማኖቷ እንድታረግ ያስገድዳታል ። የሷ ቢጤ ጭዋ ሀይማኖተኛ መስሎ በቀረባት ወንድ'ም ዳግም ትከዳለች ። ይሄ የዳግም ክህደት አጋጣሚ በታሪኩ ውስጥ ያለ ሁለተኛ አብይ ግጭት ነው ።

(. . . ሐ)

በሁለቱ የተለያዪ አበሻ ወንዶች የደረሰባት የፍቅር ክህደት የፈረንጅ ጓደኛ እንድትይዝ ምክንያት ሆናት ። ትዳር ሳይዙ አመት መቆየታቸው ምቾት ያልሰጣት ኂሩት ስትደናገጥና ስትቆጣም ይታያል ።

ፈረንጁ በሌላ አበሻ ሴቶች መነሁለሉና ለትዳር ዝግጁ እንዳልሆነ ብሎም ወደነሱ መሄድ እንደጀመረና እንደተለያዩ ታሪኩ ይተርካል ።

ቁጣዋንና ተመርኩዘን ስብዕናዋን የገመገምን እንደሆነ ከሆነ ከግዜ በኋላ የዳበረ ሀይለኛ በላይነት መንፈስ እንዳለባት ያስጠረጥራል ። ከዚህ ቀደም የየነበሩት ሁለት ፍቅረኞቿ የመጀመሪያው በደሞዝም ሆነ በትምህርት ደረጃ ዝቅ ያለና ጭምት ሲሆን ሁለተኛውንም እሺ ያለችው ድኻ የገበሬ ልጅ እንደሆነ እየማለ በነገራት ግዜ ነበር ።

-

የላይኞቹን ሶስት የወንድ ጓደኞቿን በተለያዩ በቬን ኳስ የሳልን እንደሆነ . . .

ሀ ( ከሰባት አመት በኋላ የከዳት- ማጥፋቱን ቢያምንም) ፤
ለ ( በሁለት ወራቸው የከዳት - የተሰወረ ) ፤
ሐ ( አመት ቆይቶ የከዳት - በሰላም የተለያዩ )

ሁሉም የሚገናኙት በክህደታቸው ነው ። እንደ ክህደቱ ቀለም መለያየት የተለያዩ መልሶችን ብትሰጥም መካዷ የሶስቱንም አንጓ ሴማ አንድ ያረገዋል ።

(. . . መ)

" ወለደች ፤ ከማ ? ከ'አንዱ "

ይሄ ኩርባ በመፅሃፉ ያለ የኂሩት ህይወት መደምደሚያ እና የጠቅላላው ታሪክ ፍፃሜ ሲሆን አንዲት መስመር ብቻ ይይዛል ።

በትምህርቷ ጥሩ የነበረችው ኂሩት የመጀመሪያ ጓደኛዋን የያዘችው ሁለተኛ ዲግሪ ተመርቃ ስራ በያዘችበት ወቅት እንደመሆኑ እድሜዋን ከሃያ አምስት በላይ አድርጎ መገመት አይከብድም ። በዚህ ላይ ሰባት አመት ከሁለት ወር ብንደምር ኂሩትን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ እናገኛታለን ። ይህ 'መ' ላይ ለደረሰችበት ውሳኔ እንደምክንያት ሊነሳ
ይችላል ።

-

( . . . መውጫ (ድህረ ታሪክ))

መዝጊያው የ'መ'ን ታሪክ ዲስቶርት በማድረግ 'ግን' 'አይበለውና' 'ለመሆኑስ' በሚሉ መላምቶች ደራሲው ይጠመዳል ። ቀደዳ እንደመሆኑ - ደራሲው በታሪኩ ውስጥ እንደልቡ ሲሳተፍ እና አስተያየት ሲሰጥ እናገኘዋለን ።

ሴቶች ትዳር ሳይመሰርቱ ቆይተው ልጅ የመውለጃ ግዜ ቢያልፍባቸው ስለሚገጥማቸው ነገር የሚተነብየው ይሄ ክፍል የሚደርስባትን የስነልቦናና ማህበራዊ ቀውሶች ለመዳሰስ ይሞክራል ። በትምህርታቸውና በሌሎች መስፈርቶች ከሌሎች በጉብዝና ላቅ ያሉ ሴቶች ለምን ቀድመው ትዳር እንደማይመሰርቱም አተኩሮ ይጠይቃል ።

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -

Tuesday, September 19, 2017




“ቼ በለው!” የዘመኑን መንፈስ የሣለው መጽሐፍ

(በ ዳዊት)

በእዮብ ምሕረተአብ ስለተጻፈው “ቼ በለው” የተሰኘ መጽሐፍ በሰፊው ከማተቴ በፊት በመጀመሪያ ጠቅለል ያለ ዳሰሳ፣ በወፍ በረር ልሂድበትና ከዚያ ሁለት ዋና ዋና ነጥቦችን አነሳለሁ። በኋላ ላይ የማነሳቸው ሁለት ሀሳቦች ዛይትጋይስት እና ቢጫ ናቸው፡፡ (ቀብድ ያዙልኝ)፡፡
.
ቼ በለው የሚጀምረው በምክር ነው፡፡ እንደ ደራሲው በጉራማይሌ ላውራና That is so unlike the him፡፡ “እሺ አይለውም”፤ ያ ትውልድን ያንቆለጳጵሳል፡፡ “The ጥበብ ጠራችኝ” የኢትዮጵያን የሥነ-ጥበብ በተለይም የድርሰት ሁኔታን ይተቻል፡፡ “ጎኔ ስትወሸቅ ጡቷ ነካኝ። ወይንም በድሮ ደራሲ አገላለጽ ጡቷ እንደ ጦር ወጋኝ” ይላል ለምሳሌ። “አስባለሁ” በሚለው ትረካ ውስጥ ተራኪው የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ከዓለም አቀፍ ሁኔታ ጋር እያነጻጸረ፣ ለአገሩና ለአገሩ ሰዎች ከንፈሩን ይመጣል፡፡ May Day የሚለው ታሪክ ደግሞ የዚህ ዘመን ቱሉ ፎርሳ ነው፡፡ የተዘነጋውን መደብ ዳይናሚክስ ያሳያል፡፡ ሠራተኛው መደብ ከየት ወደ የት የሚለውን ያስቃኛል፡፡
.
የመጽሐፉን ርዕስ የያዘው እና መጨረሻ ላይ የሚመጣው ትረካ ደግሞ “ቼ በለው” በፖስት ሞደርን የአጻጻፍ ስልት የተዘጋጀ ነው፡፡ ድርሰቱ የተዋቀረው በPastiche ነው፡፡ ከዚሀ በፊት የነበሩ ድርሰቶችን እየቆራረጡ በመቀጣጠል ስልት የተሠራ ነው፡፡ ሆኖም በየመካከሉ በገቡ አያያዦች እርዳታ ያልተቆራረጠ ፍሰት አለው፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ አንድም የደራሲው ድምፅ አይሰማም፡፡ የጸሐፊው የንባብ አድማስ ግን ምን ያክል ሰፊ እንደሆነ እናስተውላለን፡፡ ደራሲው ሰፊ የንባብ ልምድ ከማካበቱም በላይ መረጃን ሰብስቦ በመተንተን፣ ለነባራዊው ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል አድርጎ የማስቀመጥ አመዛዛኝ፣ የአንባቢነት ችሎታ እንዳለው ያሳየበትም ነው፡፡
.
በግል ከማውቀውም ውጪ ጽሑፉ ላይ በግልጽ እንደሚታየው፣ እዮብ ምሕረተአብ አራዳ ደራሲ ነው፡፡ ደራሲ ማለት ከፊደል ጋር ብቻ የተጣበቀ ደብተራ ሳይሆን ሕይወትንም እያጣጣመ የሚኖር ሙሉ ሰው መሆን እንዳለበት ማሳያም ነው። ኬኦስ ቲዮሪ (Chaos Theory) እና Butterfly Effect ገብቶታል፡፡ ሕይወት ማለትም የነገሮች ሁሉ ትሥሥር ውጤት እንጂ አንድ ነጠላ ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ ተረድቷል፡፡ በኑሮ የተረዳውንና ያጋጠመውን ሁሉ በልዩ የአተራረክ ችሎታና በአዝናኝ አቀራረብ፣ “ቼ በለው” በተሰኘው መጽሐፉ አንድም ሳያስቀር ሰጥቶናል፡፡
.
“ቼ በለው” ቋንቋው ቀላል፣ ግልፅና ሂዩመረስ ነው፡፡ በቀላል ቋንቋውና በዚቀኝነቱ ተከልሎ ቁምነገሩን መሳት ግን ትልቅ ስህተት ነው፡፡ የቋንቋው ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ጉራማይሌ መሆኑን መጥቀስ ያስፈልጋል፤ ይሄ በእኔ አመለካከት እጅግ ተገቢ ነው፡፡ ስለ አማርኛ ሥነ ጽሑፍ እያተትኩ፣ ጉራማይሌ ቋንቋን እንዲህ ማዋደዴ ለምን እንደሆነ ወደ በኋላ እመለስበታለሁ፡፡
ቢጫው መጽሐፍ
ከላይ እንደ ቀብድ ካስያዝኳቸው ርዕሶች አንዱ “ቢጫ” ነው፡፡ እሱን እናውራ፡፡ ቢጫ የአገራችን ቀለም ነው፡፡ ባንዲራችን ውስጥ መሀል ላይ አለ። ኢትዮጵያ የሚለው ቃል መካከል “ዮጵ” የሚል ቃል አለ፡፡ ያልተነጠረ ወርቅ ማለት ነው፡፡ ቀለሙም ቢጫ ነው፡፡ የዘመናችን መጀመሪያ የሆነው መስከረም ወር በቢጫ አደይ አበባ የተሸፈነ ነው፡፡ ቢጫ ቀለም የአገሪቱ ማዕከል እንደሆነ ሁሉ የ”ቼ በለው” መጽሐፍ ማዕከልም ቢጫ ነው፡፡ “ቼ በለው” ቢጫ መጽሐፍ ነው፡፡ ስለ ምን እንደዚህ አልኩ? አብረን እንቀጥል…
.
“ቢጫ” የሚል ርዕስ በተሰጠው ትረካ ውስጥ “ትዝታ ዘ ቢጫ ቀለም” የሚል ምዕራፍ አለ፡፡ ትውስታና ቀለም እንዴት ተሰናስለው እንደሚፈስሱ ያሳያል… ተራኪያችን ወዳጆቹ ቤት ሄዶ፣ ባልና ሚስት ቢጫ ጄሪካንን መነሾ ያደረገ ጭቅጭቅ ሲጀምሩ ሲያይ፤ ስለ ቢጫ ቀለም ያለውን ትውስታ ሁሉ የሚበረብርበት ምዕራፍ ነው…. የሚያስታውሰውም ይሄን ነው… “ቢጫ ቀለም ሲባል የሼል ማደያ ምስል - Western Union - የሀምሳ ብር ኖት - የፀሐይ ብርሃን ያጣ ሣር - የመነኩሴ ቆብ - እርድ የበዛበት መኮሮኒ - National Geography - ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ - የበላይ ተክሉ ኬክ ቤት ተቆራጭ - ደምበል ሕንጻ - DHL - የሸገርን ባቡር የሚነዳ ቻይናዊ ፊት - የስዕል መምህራችን ʻከሰንደቅ አላማችን ቀለማት መካከል መሥራች ቀለም ያልሆነው የቱ ነው?ʼ ብሎ ጠይቆኝ ʻቢጫʼ ብዬ በመመለሴ እንደ ሀገር ክህደት ቆጥሮት የኮረኮመኝ ኩርኩም - ለሊያ ልጅ ለናፒ ልደት የገዛሁላት ሸራ ጫማና - የአብዛኛው ኮንዶሚኒየም ሳሎን ቤት ቀለም ይታወሰኛል፡፡”
.
ይሄን ሁሉ የትውስታ ሰልፍ ደርድሮ፣ በመጨረሻም ገጠር ለስራ ሲወጣ ቧንቧ ስር ተኮልኩሎ የሚያየውን ቢጫ ጄሪካን ያሳየናል፡፡ አደይ አበባንም ያስታውሳል፡፡ አበባውን አስታክኮ አንደኛ ደረጃ አብራው የተማረችው አደይ የተባለች ልጅ ትዝ ትለዋለች፡፡
.
ተራኪውም ሆነ እኔ፣ ይሄን ሁሉ የትውስታ ጋጋታ የምናቀርብላችሁ ያለ ነገር አይደለም፡፡ ተራኪው ቀስ ብሎ ወደ ቀለም ሥነ ልቦና (psychology of color) ሊገባ ነው፡፡ እኔ ደሞ ተያያዥ ስለሆኑ ነገሮች ላነሳሳ ነው፡፡ ተራኪው የቢጫ ቀለምን ሥነ ልቦናዊ ትዕምርት ለመረዳት፣ የቀለም ሥነልቦናን ተጠቅሞ ትርጓሜውን እንዲህ ያስነብበናል……
“Yellow is truly joyous and radiant color. It exudes warmth, inspiration and vitality. It is the happiest of colors. Yellow signifies communication, enlightenment, sunlight and spirituality. If your treasured color is yellow, you look forward to the future. Intellectual, highly imaginative and idealistic, you have a cheerful spirit and expectations of greater happiness”
.
ቢጫ ቀለምን ለመግለጽ የተጠቀሟቸውን ዋና ዋና ገላጭ ቃላት ጎን ለጎን ብንደረድራቸው የምናገኘው፤ “ቼ በለው” የተባለው የእዮብ ምሕረተአብ መጽሐፍ ትክክለኛ መገለጫዎችን ነው፡፡ ልክ እንደዚህ…. Joyous, radiant, warm, communication, enlightenment, looking forward to the future, intellectual, highly imaginative, idealistic, cheerful spirit and expectations of greater happiness. የቼ በለው መጽሐፍ ምንነት ይሄው ነው፤ ቼ በለው Joyous ነው። ቼ በለው radiant ነው፡፡ ቼ በለው intellectual እና imaginativeም ነው፡፡ ለዚህም ነው “ቼ በለው ቢጫ መጽሐፍ ነው” ብዬ የጀመርኩት፡፡
.
ደራሲው እዚህ እና እዚያ ዐሥር ጊዜ “ቢጫ ጄሪካን” ቢላችሁ አንድምታ አለው፤ አንድም የኢትዮጵያ ምድር ከዚህ በኋላ በቢጫ ጄሪካን እንጂ በአደይ አበባ አለመሸፈኑን በማስተዋሉ፤ አንድም ደሞ የልቦለዱን አውድ ለመገንባት እንደ ሞቲፍ ሊጠቀምበት፤ አንድም አጨራረሱን ሊያሳምር ነው። ቢጫ ጄሪካን ቀላል አይደለችም፡፡ አገሪቱ ላይ ያላት ተጽዕኖ በዝርዝር ቀርቦልናል - “የቢጫ ዘይት ጄሪካን እና የአገሪቱ እርምጃ” በሚል ፌዘኛ መሳይ ርዕስ፡፡
“…ሸኖ ላይ የሰላሌ ኦሮሞ ወተቱን በአባ ዱላ ወደ አዲስ አበባ የሚልከው በነዚህ ቢጫ ጄሪካኖች ነው፡፡ የደንበጫ ጎጃሞች የግብጦ አረቄን ጠምቀው የሚያስቀምጡት በእንስራ አይደለም፤ በዚህ ቢጫ ጄሪካን ነው፡፡ ከጅቡቲ ወደብ እስከ ገዳማይቱ ይሄንን ቢጫ ጄሪካን በኮንቲነርና በግመል ተጭኖ በገፍ ሲገባ ታየዋለህ፡፡ አዲስ አበባ የሚገኙ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ አራተኛ ፎቅ ተከራይቶ ቢጫ ጄሪካን የሌለው ሰው የለም፡፡ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የቦኖ ውሃዎች ላይ ረጅም ወረፋ ካየህ፣ የተደረደረ እንስራ ወይም ሌላ አይነት ከለር ያለው ጄሪካን በብዛት አይገጥምህም - ይሄው ቢጫ ጄሪካን እንጂ!”
አሁንም ልብ በሉ፤ ደራሲው ይሄን ሁሉ የሚለው በወለፈንድ ሲዘባርቅ አይደለም፡፡ ነገር የሚፈተፍተው ወደ ዛሬ መልሶን፤ ሁኔታውን ካለንበት ነባራዊ እውነታ ጋር ጠቅልሎ ሊያጎርሰን ነው፡፡
.
እዮብ ቢጫ ጄሪካን ተሸክሞ እንደ ጦስ ዶሮ ስንትና ስንት ቦታ ከተሽከረከረ በኋላ ማረፊያውን የሚያደርገው ጌቱ ገለቴ ላይ ነው፡፡ ጌቱ ገለቴ የቢጫ ጄሪካን አባት፤ ኦሎምፒያ አካባቢ ያለው የጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር ባለቤት ነው፡፡ በዚያን ዘመንም ጌቱ የተቀሸበ ባለ ሀያ አምስት ሊትር ዘይት ከታይላንድ አገር አስመጥቶ ያከፋፍል ነበር፡፡ ዛሬ ግን “የሆነች ማኖ ነክቶ” ከአገር የወጣ በኢንተርፖል የሚፈለግ ባለሃብት ነው፡፡ ደራሲው የጌቱን ጉዳይ በአጭሩ አውስቶ፣ መንግሥትን ጎሸም ያደርጋል፡ “መንግሥት የዘይትንና የስኳርን ዋጋ ልተምን ብሎ ቡራ ከረዩ ሲል የዚህን ባለ ቢጫ ጄሪካን የታይላንድ ዘይት መቆጣጠር ግን ተስኖታል”፡፡
.
የቼ በለው ደራሲ ሕይወትን ለመዘገብ ቢጫ ቀለምን ሞቲፍ (motif) አድርጎ መምጣቱ ከተራ አጋጣሚነት ያለፈ ነገር እንዳለ ያስታውቃል። ምክንያቱም እንደ ቢጫ ቀለም ግራ የሚያጋባ ትእምርት ያለው ሌላ ቀለም የለም፡፡ ዓለም ብሩህ እና ጸሊም እንደሆነችው ሁሉ ቢጫ ቅዱስም እርኩስም ነው፡፡ እናም ክፉና ደግ ተዋህደው፣ አንድ አካል ሆነው የሚኖሩባትን ዓለም ለመሣል፣ ቢጫ ቀለምን መጠቀም የመሰለ ተገቢ ምርጫ ሊኖር አይችልም፡፡ ስለ ቀለማት ትእምርትና አመጣጥ በሰፊው የመረመረችው Victoria Finlay ስለ ቢጫ ቀለም እንዲህ ትላለች፡ “No color has a neat unambiguous symbolism, but yellow gives the most mixed messages of all. It is the color of pulsating life—of corn and gold and angelic haloes—and it is also at the same time a color of bile, and its sulphurous incarnation it is the color of the Devil” (Color: A Natural History of the Palette, pp 202) በግርድፉ ስንተረጉመው፤ “እንደ ቢጫ ቀለም ያለ የተደበላለቀ ስሜት የሚፈጥር ቀለም የለም፡፡ ቢጫ የሕይወት ቀለም ነው - የበቆሎ፣ የወርቅ እና የቅዱሳን አክሊል፤ ቢጫ በሌላ መልኩ የክፋት ቀለም ነው፤ ቢጫ ቀለም ያለው ሰልፈር ለምሳሌ የሰይጣን ቀለም ነው”፡፡ ታዲያ የእግዜርም የሰይጣንም የሆነችው አለም፣ ከዚህ ባለ ብዙ ገጽ ቀለም ሌላ በምን ትሳላለች? ቼ በለው የተሰኘው መጽሐፍስ ቅድስና እና እርኩሰት በደቦ የነገሡበትን ዘመናችንን ለመግለጽ፣ ማዕከሉን ቢጫ ከማድረጉ በላይ ተገቢ ነገር አለን?
.
“ቢጫ” የሚል ርዕስ ባለው ትረካ ውስጥ ጉልህ ቦታ የተሰጣትን ቢጫ ጄሪካን ደራሲው አናሎጂ ለመፍጠርም ተጠቅሞባታል፡፡ የዚህን ታሪክ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀጾች እንመልከት። የመጀመሪያው እንዲህ ይላል… “ጋን፣ እንስራና ማሰሮም ወደ ቀድሞው ስፍራቸው አይመለሱም። ወደ ሰባ ሚሊዮን ከሚሆነው የገጠሩ ህዝብና በርኸኛው እንስራንና ማሰሮን በዚህ ክብደት በሌለው ግን ጠንካራ በሆነ ውሃ መቅጃ እየተኩት ነው፡፡ የሴት ልጅ ወገብም ከከባዱና ከተሰባሪው ገል ተገላግሏል፡፡ ዕድሜ ለጌቱ ገለቴ - ዕድሜ ለቢጫ ጄሪካኑ”፡፡
.
በዚህ ታሪክ ውስጥ የሚገኘው ተራኪ የሆነ መስሪያ ቤት ጉዳይ ሊያስፈጽም ሲሄድ ያገኛት አንደኛ ደረጃ አብራው ስለተማረችው አደይ ስለተባለች ልጅ ሲነግረን ነበር፡፡ ሁለተኛው አንቀጽ የሚያሳየን የእሷን መጨረሻ ነው፡፡ እንዲህ ይላል… “ያ! የሙዝ ቅርጽ የነበረው፤ ያ! የብርጭቆ ቂጥ መነጽር ዓይኗን ምስር ያስመሰለው፤ ያ! ቡጉንጅ የሞላው ድንጉጥ የአደይ ፊትም፤ መቼም መቼም አይመለስም”፡፡ የጄሪካኑ እና የአደይ ሕይወት ተነጻጻሪ ሆነው ቀርበዋል፡፡ ሁለቱ የሚገናኙበት ነጥብ ደግሞ ቢጫ የተሰኘው ቀለም ነው፡፡ ቢጫ ቀለም እንደዚህ ታሪኩንና አጨራረሱን ለማሳመር ተጠቅሞበታል፡፡ በእርግጥ ደራሲው በአጨራረስ የሚታማ አይደለም፡፡ እንዲያውም የሚደነቅ የአጨራረስ ችሎታ አለው፡፡ ለዚህም አብነት የሚሆነን “መርዓ” የሰኘው ታሪክ ነው፡፡
.
መርዓ የሚጀምረው በሆነ የትግርኛ ዘፈን ነው። ባለ አራት መስመር የዘፈኑ ግጥም እንጂ ትርጉሙ አልተሰጠንም፡፡ “ከም ኤርትራ አዴታት መንም አይወለዳ” ይላል የመጨረሻው ስንኝ፡፡ ባይገባንም ይሁን ብለን እናልፈዋለን፡፡ አስገራሚው ነገር ትርጉሙን የምናገኘው የታሪኩ መቋጫ ላይ መሆኑ አይደለም፡፡ አስገራሚው ነገር ትርጉሙ ከኋላ መምጣቱ፣ ለአጨራረሱ የሰጠው ክብደት ነው፡፡
.
መርዓ በትግርኛ ሰርግ ማለት ቢሆንም፤ ተራኪው የሚያሳየን ያለውን የብሔር ብሔረሰብ ውጥረት ነው፡፡ የአንዱን የተጨቆንኩ ለቅሶ፣ የአንዱን የተበደልኩ ዋይታ፣ የሌላውን የበላይነት ትምክህት። ይሄን ሁሉ አስተውሎ ተራኪያችን በሰርግ ቤት መሀል እንዲህ ይተክዛል… “ይሄ እርጉም አህጉር - ይሄ ከይሲ ጥቁር ሕዝብ - ይሄ ችጋር የሚጠበጥበው የአፍሪቃ ቀንድ - ይሄ ጦርነት የማያጣው ቀንዳም ክፍለ አህጉር - ይሄ ደዌና ቸነፈር ያቀረጨጨው ጊንጥ ሕዝብ - በዘር፣ በክልል፣ በድንበር የተከፋፈለ - ሊባላ ከጫፍ የደረሰ - ድሮም፣ አሁንም፣ ወደፊትም ራሱን ችሎ በልቶ ማደር የማይችል አፍሪቃዊ!... እውነትም The Hopleless Continent!”፡፡
እዮብ በጉራማይሌ ቋንቋው ታሪኩን እንደዚህ ይፈጽመዋል… “(Afterall) ʻዘርህ ከአሜሪካዊያን፣ ከአውሮፓውያንና ከእስያውያን ይበልጣልʼ የሚል ዘፈን፣ (አፍሪካም የለበትም) ከውስኪና ከፊያሜታ ጋር ተጨምሮ ሌላም ያስረሳል፡፡ Self Denial… Identity Crisis…. Narrow Identity… Grey Nationalism… Greed… Pessimism.” እንደዚህ አይነት ውብና ጠንካራ አጨራረስ የሚታየው ጥቂት የፈጠራ ስራዎች ብቻ ላይ ነው፡፡
.
ዛይትጋይስት (Zeitgeist)
ቃል ወደ ገባሁላችሁ ወደ ሁለተኛው ሀሳብ ልቀጥል፡፡ ዛይትጋይስት፡፡ ዛይትጋይስት ከሁለት ቃላት የተሰራ የጀርመንኛ ቃል ነው፡፡ “ዛይት” ማለት ጊዜ ሲሆን “ጋይስት” ደሞ መንፈስ ነው፡፡ የዘመኑ መንፈስ እንበለው፡፡
.
የዘመኑን መንፈስ ለመዘገብ የዘመኑን ቋንቋ መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ለዚያም ነው ከላይ “ቼ በለው” ላይ ያለው የቋንቋ አጠቃቀም ጉራማይሌ መሆኑ ተገቢ ነው ያልኩት፡፡
.
ከቋንቋ አጠቃቀም ውጪ የዘመን መንፈስ እንዴት ይዘገባል? እንደዚህ ነው፡፡ ቼ በለው ውስጥ ሁሉም ታሪኮች ውስጥ ማለት ይቻላል እየተደጋገመ የሚመጣ ጭብጥ አለ፤ ይሄውም ገንዘብ ነው፡፡ ይሄም የዘመኑ መንፈስ ዋና መለያ ነው፡፡ ለምሳሌ I wanna be a Billionaire በሚል ግልፅ ርዕስ የተቀመጠው ታሪክ አንድ ማሳያ ነው። በአብዛኞቹ ታሪኮች (ሁሉም ማለት ይቻላል) እየተመላለሰ የሚመጣ ጭብጥ ነው፡፡ መቼም ውሻ ውሻን የሚበላበት የካፒታሊዝም ሥርዓት ውስጥ እየኖርን፣ ካሽ የሁሉም ነገር ቁልፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ደራሲው በእርግጥ የብዙ ነገር ቅይጥ የሆነውን “የኛን ካፒታሊዝም” የሚጠራበት አባባል አለው - “ሚስቶ ካፒታሊዝም”፡፡ በአማርኛ ልቦለድ ትልቅ ድርሳን የሆነው “ፍቅር እስከ መቃብር” ዘመኑን በማሳየቱ፣ ዘመን ተሻጋሪ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ይወደሳል፡፡ የእዮብ ምሕረተአብ “ቼ በለው”ም የዘመኑን መንፈስ በቃላት ሥሎ በማቅረቡ የዘመናችን ፍቅር እስከ መቃብር ነው ብል አላጋነንኩም፡፡ ልዩነቱ ቼ በለው ውስጥ ያለው ጉዱ ካሳ ደራሲው ራሱ መሆኑ ነው። አዎ፤ እዮብ ምሕረተአብ የዘመኑ ጉዱ ካሳ ነው፡፡ እዮብ ኑሯችንን ያለ ፍርሃትና ያለ ሃፍረት ያወራዋል፤ የሚያወራውን ይጽፈዋል፡፡ አይፈራም፤ አያፍርም፡፡ የማይደፈር የተባለውን ደፍሮ ይነግረናል (ወይም በራሱ አባባል ይቀድልናል)፡፡ ድርሰቱ (በእሱ አባባል ቀደዳዎቹ) ዛሬን ያሳያሉ፡፡ ደራሲ እዮብ ቀጥተኛ ነው፡፡ ሆኖም ይሄ ቀጥተኛነቱ የአንዳችን ሕይወት ከሌላኛችን የተሳሰረበትን ቀጭን መስመር ከማስተዋል፤ ትስስራችን የቆመበትን ተዋረድም ከመመርመር አያግደውም፡፡ አብዛኛውን ጊዜም ቀላል በመሰለ ንጽጽሮሽ እልፍ ነገር ይነግረናል፡፡ መርዓ የተሰኘው ታሪክ ላይ ለምሳሌ ጋሽ ካህሳይ የተባሉ የአንደኛ ደረጃ ሒሳብ አስተማሪ አሉ፡፡ “አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ኤለመንተሪ ተማሪ ሆነን ሒሳብ ያስተማሩን፣ በግማሽ ትግርኛና በግማሽ አለንጋ ነበር” ይላቸዋል ተራኪው፡፡ በስንት ችግር ውስጥ አልፈው ዛሬም በድህነት ይኖራሉ፡፡ “ሰርክ እንደተጫወቱ፤ ሁሌ እንደቀለዱ ነው፡፡ ምንም አልተቀየሩም”፡፡ ታዲያ እዚያው ታሪክ ላይ እንደ ማነጻጸሪያ ሆኖ የቀረበ ታናሽ ወንድም አላቸው፡፡
.
“ታናሽ ወንድማቸው ደሞ ሌላ ታሪክ ያለው ሰው ነው” ብሎ ይጀምራል ትረካው፡፡ ታናሽዬው ታጋይ ነበር፡፡ አዲሳባ ገብቶ ኑሮና ብልሃቱን መታገል ቀጠለ፡፡ ድህነትን “አቸንፎ” ኢንቬስተር ሆነ፡፡ “ምሥራቅ በር ዱከም ቁርጥ ቤት፣ ቶቶት ክትፎ፣ ጽጌ ሽሮ እና ቃተኛ ሰርክ የማይጠፋባቸው ሥፍራዎች ሆኑ፡፡ ሞሮኮ ባዝ እና ኤሮቲክ ማሳጅ ሆቢው ሆኑ። በየቀኑ ውስኪ ያወርዳል፡፡ በግልፅ ከብዙ ሴቶች ጋር ይማግጣል”፡፡ ይሄ በቀላሉ የተቀመጠ የዘመኑ ቀለም ነው፡፡ ዘመንን መሣል ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ደራሲ እዮብ የከፈለው ዋጋ ደግሞ ከሁሉም መጣላትን ነው፡፡ ምርጥ ደራሲ ከገዛ ፈሱ ጭምር መጣላት አለበት፤ የቼ በለው መጽሐፍ ደራሲ ያደረገውም ይሄንኑ ነው፡፡ ከማንም ጋር ስምሙ አይደለም፡፡ ሁሉንም ይነቁራል፡፡ ሁሉንም ይተቻል፡፡ ሁሉም ላይ “ሙድ ይይዛል”፡፡ ፖለቲከኞች፣ መንግስት፣ ተቃዋሚ፣ ባለሃብት፣ ደሃ፣ ጸሐፊዎች፣ ጋዜጠኞች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ብሔር ብሔረሰብ፤ ሐይማኖት፣ ፌሚኒዝም፣ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ወዘተ…
.
“የዘፈን ምርጫ” ላይ አላሙዲ እና ኢንጂነር ይልቃል ተፎግረዋል፡፡ “The ጥበብ ጠራችኝ” ደራሲዎችን ይነቁራል፡፡ “ስብሰባው” እና መርዓ ብሔር ብሔረሶቦች ላይ ይቀልዳል፡፡ የመንግስት ጋዜጠኞች እና ተመራጭ ገጸ ባሕሪዎቻቸው - ማለትም አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ሁለቱም ድህነት የሚሉት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሆነው ተስለዋል፡፡ በዚህ ዘመን አለ የተባለ የማሕበረሰብ ክፍል፤ ዛሬ ላይ የሚገኝ የአኗኗር ዘይቤ ሁሉም ተዳርሰዋል፤ ሁሉም ተጎሽመዋል፡፡
.
ለምሳሌ ደራሲው የብሔር ብሔረሶችን ጉዳይ skillfully mock ከሚያደርግበት ክፍል አንዱ “ስብሰባው” በተሰኘው ታሪክ ውስጥ ይገኛል፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ መስሪያ ቤታችን ውስጥ የጀበና ቡና መጀመር አለበት የሚለውን ሀሳብ ተመካክሮ ለመወሰን ሰራተኛው በሙሉ ይሰበሰባል፡፡ የመስሪያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ ጉዳዩን ጠላቶቹን ለመምታትና ወዳጆቹን ለማበልፀግ ይጠቀምበታል፡፡ ዋና ዋና ከሚባሉ ብሔሮች ወካይ እንደሆኑ በግልጽ የሚያስታውቁ ገጸ ባሕሪዎች እየተነሱ ይናገራሉ፡፡ ጉዳዩ ከቡና ወደ ፖለቲካ ይቀየራል፡፡ ከጀበና ወደ ማንነት ጥያቄ፡፡ ቆይቶ ሌላ አጀንዳ ይጨመራል - ፌሚኒዝም፡፡ ይሄንን ክፍተት ተጥቅሞ፣ ስራ አስኪያጁ፣ ያንንም ያንንም ጃስ ካለ በኋላ “ችግሩ የጀበና ቡና አለመኖሩ ሳይሆን የመስሪያ ቤቱ ካፌ ጥሩ አገልግሎት በማይሰጥ ድርጅት እጅ ውስጥ በመሆኑ ነው” በሚል ሰበብ ጉዳዩን ለግል ጥቅሙ ሲያውለው ይታያል፡፡ “ሴቶችን ለማበረታታት” በሚል “ጆካ”፣ ካፌውን ለአንዲት ዘመዱ ይሰጣታል።
“የመስሪያ ቤታችን ስራ አስኪያጅ እጅግ ዴሞክራት ነው” ብሎ የጀመረው ታሪክ መጨረሻም ላይ በአጽንዖት ጭምር ይደግመዋል፡፡ እንደዚህ…
“እውነቴን ነው - የመስሪያ ቤታችን ስራ አስኪያጅ ዘመኑ የገባው ʻዴሞክራትʼ ነው”
ይሄ ዘመናችን ነው፡፡ ይሄ አሁን ነው፡፡ ይሄ ሕይወታችን፤ ኑሯችን ነው፡፡ “ቼ በለው”ን ጠቅለል ባለ መልኩ ስገልጸው፣ የሸገር ከተማ አንትሮፖሎጂና ኮስሞፖሊታን ተረክ ነው፡፡ ከላይ ከላይ የሚታየውን ሳይሆን፤ ውስጥ ለውስጥ ይህቺን ከተማ (by extension ይቺን አገር) ማን እንዴት ባለ ብልሃት እንደሚመራት እያሳሳቀ የሚያሳይ የዘመናዊ አዲስ አበባ መምሪያ መጽሐፍ (guidebook) ሆኖ ሊያገለግልም ይችላል፡፡ ነገሮች ከላይ እንደሚታዩት እንዳልሆኑ የሚያስረዳ ውስጠ-አዋቂ መረጃ ያቀብላል፡፡
-
“ቼ በለው” ውስጥ በግልፅ እና በደማቁ የተሣለው የዘመኑ መንፈስ ነው፡፡

Wednesday, April 26, 2017

የዘመኑ ሴቶች መጣበሻ ክራይቴሪያ (ለወንዶች ብቻ)



[Mahi]

• • • • • •

ማስታወቂያ!!
ማስታወሻ!!
ለስራ ፈላጊዎች!!
ይሄን ያውቁ ኖራል!!
ይልሃል ባለ እድል!!!

• • • • •

"ብርዱን ኣስመልክቶ የወጣ ፍላጎትን መግለጫ"

(በፈለጉት ርእስ ማንበብ ይችላሉ)

.
ጉዳዩ:~ የፍቅር ኣጋርን መፈለግ
ፈላጊ:~እኔ
ፆታ:~ወንድ!!
እድሜ:~ከ27~34
አቋም:~ ልክ ያለው....ጡቱ ከኔ ጡት ማይበልጥ .....ኣጠገቤ ቁጭ ብሎ ወደሌላ ኣቅጣጫ እንዳላይ ማይከልለኝ....ማያሳምመኝ....

Tuesday, April 25, 2017

ኃያሉ ሠው

     


(ክቡርነታቸው)

-- ከዱሮ ጀምሮ Arrogant ናቸው - እንደ ወይራ፡፡

-- አንዳንድ እሳቤዎቻቸው አለቅጥ የተጋነኑ፣ ሆነ ብሎ ነገር ቆልማሚ እና የአሁንን (የዘመኑን) ነባራዊ እውነታ ባላየ የዘለሉ ናቸው፡፡
 
-- አሁን ላይ ያሉ መልካም መሻሻሎችን በጥቂትም  እውቅና አይሰጡም፡፡

-- አንዳንድ አቋማቸው አይመስጠኝም፣ አልስማማበትም፡፡

(ግን፣ ግን፣ ግን)

-- ክቡርነታቸው ሶስቱንም መንግስታት ወጥረውና ተጋፍጠው ሲቃወሙ ኖረዋል፡፡

-- በሰማንያ ምናምን አመት ዕድሜው ደፍሮ እውቀቱን እና እሳቤውን ሳያሰልስ የሚጽፍ ምሁር ኖሮን አያውቅም፣ የለንምም!

-- የነጮች ሎሌ፣ ወይንም የጽንፈኛው ዳያስፖራ አፈ ቀላጤ ሆነው አያውቁም፤ አሽቄ አይደሉም!!

-- የ65/66ቱን ረሃብ ቀድመው ለዓለም መንግስታት ያሳወቁትና ያጋለጡት እርሳቸው ናቸው፡፡ ጆናታን ድምቢልቢ በሳቸው ሪፖርት መሠረት ነው መጥቶ ዝነኛውን የሆረር ዶክመንተሪ የሠራው፡፡

-- ከጠረፍ ጠረፍ ዞረው መሬት ለክተው የዚህን አገር ካርታ (Atlas) ያዘጋጁ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡

-- “ጦርነት እና ነውጠኛ አብዮት ለዚህች አገር  መፍትሄ አይሆንም፣ ሆኖም አያውቅም” የሚለው ቀጥተኛ አቋማቸው ከጥንት እስካሁን አልተቀየረም፡፡ አንድ ሰው 60 አመት ሙሉ በአቋሙ ወጥ ሲሆን ማየት በራሱ ትልቅ ክላስ ነው፡፡
(መጽሃፎቻቸውንና ጽሁፎቻቸውን በሙሉ አንብበውና ፍረድ!)

-- ያልተዝረከረከ የአመንክዮ (Reasoning) አሰዳደር፣ እንዲሁም ጥልቅ ሃሳብን  በቀላል አማርኛ መግለጥ ለሳቸው የተሠጠ ትልቅ የስነጽሁፍ ክህሎት ነው፡፡ (“. . . ወይ እኔ ቂል ነኝ፣ ወይ እሱ ቂል ነው” የሚል አገላለጽ አይመስጥም?)

From Eurocentrism to Ethiocentrism

 Maimire Mennasemay (PhD)

[ Dr. Messay Kebede's thoughtful commentary on Gebrehiwot's major work, Mengistna ye Hizb Astadadar, published on this forum, draws our attention to the deleterious role that "Eurocentrism" has played in modern Ethiopia. This essay links to Messay's concern and considers what kind of perspective could restore to Ethiopians the self-confidence and creativity that have so often marked their history. ]

Monday, April 24, 2017

አሰፋ ጫቦ ቃለ መጠይቅ


አሰፋ ጫቦ - ከ'ያ ትውልድ' ብቸኛ የሚታመነው ሰው በሞት ተለየን



(ጋሽ አሰፋ ጫቦ ማን ነው?)

* * * * *

አቶ አሰፋ ጫቦ ከአባቱ ከጫቦ ሣዴ ሃማ ያሬና ከእናቱ ከማቱኬ አጀን ከተራራ አናት ላይ ከሚገኝ ሜዳማ ቦታ ላይ ጨንቻ ከተማ ነው የተወለደው፡፡ከጋሞ ሰንሰለት ተራራዋች አንዱ ጫፍ ላይ የሚገኝ ጠረጴዛ ነው ይላታል ጨንቻን ሲገልጣት  ከ2-6ኛ ክፍል እዚያው ጨንቻ የተማረ ሲሆን በዘጠኝ ዓመቱ የጨንቻ ገብርዔል ዲያቆን በመሆንም አገልግሏል በድቁናው ባገኘው ካፒታልም ጥቂት የዶሮና የበግ ግልገል ገዝቶበታል ሐሙስ ሐሙስን እየጠበቀ ኤዞ ገበያ ዶሮና እንቁላል አየነገደ ይውል ነበር ከእነሱም ውስጥ ት/ቤት ድረስ እየተከተሉ ያስቸግሩት የዶሮና የበግ ግልገልም ነበረው እንደፈረንጆቹ pet መሆናቸው ነው፡፡ የ8ኛ ክፍል ትምህርቱን በሻሸመኔ በኃላ ታሪኩን ሲያውቅ ስሙን ካላስቀየርኩ ብሎ ከታገለበት ከአጼ ናኦድ ት/ቤት ከ39 ተማሪዎች አንዱ በመሆን ነበር የተከታተለው

   የተዋቀረበትን ዋልታና ካስማ ያየበት ቆይታው በጋሞ ውስጥ ካሉ 40 ከሚሆኑ ‹ካዎ›ች አንዱ በሆኑት በዘመዱ በቀኛዝማች ኢሌታሞ ኢቻ ቤት በኖረበት ወቅት ነበር፡፡

Sunday, April 23, 2017

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ - (አዱኛ ሌሊሳ)


(By: Adugna Lelisa Sime)

* * * * *

ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከተ አጭር መግለጫ
ሚያዝያ 14 ቀን 2009ዓም
.
በቅርቡ አንዳንድ የአገራችን ክልሎች(በተለይም የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች) የአገሪቱን ህገ መንግሥት ባልተጣረሰ መልኩ ኢኮኖሚያቸውን ለመገንባት፣አቅማቸውን ለማሳደግ እና የህዝቦቻቸውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያከናወኑ ያሉትን ተግባራት የሸነግ ስብስብ በትኩረት የሚመለከት እና  የሚደግፍ ቢሆንም ይህ አካሄድ በክልሎች መካከል አላስፈላጊ ፉክክር እንዳያመጣ እና አገራዊ አንድነቱን የበለጠ ስጋት ላይ የሚጥል እርምጃ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ  ከወዲሁ አበክረን ለማሳሰብ እንወዳለን።

Remembering Prince Alemayehu

(By: Wayne Edward Maddock)

* * * * *

Remembering Prince Alemayehu: The First Ethiopian Adoptee?
.
Today is the birthdate of the late Dejazmatch Alemayehu Tewodros, born on this date on April 23, 1861.
Prince Alemayehu was the son of late Emperor Tewodros II, who ended his life by suicide on Easter Day 1868 when British forces entered his fortress in Ethiopia to rescue a group of British missionaries and diplomats.
.
Prince Alamayehu was brought to Britain under British care. Prince Alamayehu died of illness at age 18 on November 14, 1879 and was interned on the grounds of Windsor Castle .

“በነውጠኛ አብዮት ሳይሆን፣ በማህበራዊ ለውጥ እንታመናለን!”